Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው የእኔ ፡ ጌታ ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው ማነው ፡ የሚመስለው ፡ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ማነው ፡ የሚያክለው ፡ እርሱ ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ አዎ አዝ፦ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፪x) በምድር ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ገነው ፡ የነበሩ እጅግ ፡ የከበሩ ፡ ደግሞም ፡ የተፈሩ ብርቱ ፡ ሃያላኖች ፡ ጠቢባን ፡ ወድቀዋል ብዙዎች ፡ ነገሥታት ፡ ወድቀው ፡ ተረስተዋል የእኛ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ዛሬም ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ጉልበቱ ፡ ሳይደክም ፡ አለ ፡ በዙፋኑ ፡ በዙፋኑ አለ ፡ በዙፋኑ ፡ አዎ መቃብር ፡ ፈንቅሎ ፡ ድል ፡ ነስቶ ፡ የተነሳ እርሱ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፪x) የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ አዎ አዝ፦ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፪x) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፫x) ናቡከደነጾር ፡ ምስል ፡ አሰራና ስገዱ ፡ አላቸው ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ አለና ለምስሉ ፡ ከቶ ፡ አንሰግዱም ፡ ያሉ እነሲድራቅ ፡ ታስረው ፡ በእቶኑ ፡ ተጣሉ ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ሆኖ ፡ ቢነድም ፡ እሳቱ እርሱን ፡ የታመኑ ፡ አሸንፈው ፡ ወጡ ፡ ሃሌሉያ ድል ፡ አድርገው ፡ ወጡ [1] የነሲድራቅ ፡ አምላክ ፡ አሁንም ፡ ይሰራል ስሙን ፡ ለሚጠራው ፡ ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ሃሌሉያ ከሞትም ፡ ያድናል ፡ አዎ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አሃ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኦሆ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ጌታ (፪x) ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ጌታ (፫x) በጸናችው ፡ እጁ ፡ ህዝቡን ፡ አወጣቸው [2] ባሕሩን ፡ አሻግሮ ፡ በድንቅ ፡ መራቸው [3] ከኋላም ፡ ከፊትም ፡ ሆኗቸው ፡ ከለላ ተስፋውን ፡ ወረሱ ፡ ቃሉንም ፡ አጸና [4] ለእኔማ ፡ አባቴ ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ አምነዋለሁ ቢጐድልም ፡ ቢሞላም ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው በቁሳቁስ ፡ ነገር ፡ እኔ ፡ አልመዝነውም ከሁሉም ፡ ይልቃል ፡ ጌታ ፡ እኩያ ፡ የለውም ፡ አባብዬ እኩያ ፡ የለውም ፡ አዎ አዝ፦ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፪x) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፫x) እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (በዙፋኑ ፡ ላይ) የእኔ ፡ ጌታ ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ነው (ኦ ፡ ላይ ፡ ነው) ማነው ፡ የሚመስለው (የእኔ ፡ ጌታ) ፡ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (ማነው ፡ ማነው) ማነው ፡ የሚያክለው (ኢየሱሴን) ፡ እርሱ ፡ የበላይ ፡ ነው ፡ (አዎ ፡ አዎ) አዝ፦ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ (በላይ ፡ በላይ) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (በላይ ፡ ነው) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (በላይ ፡ በላይ) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፪x) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ በላይ (፫x)