Loading
Singer
ሰላምህ ፡ በዝቶልኛል ፡ አንተን ፡ ከአገኘሁ ፡ ጀምሮ ሕይወቴ ፡ ተለውጧል ፡ ተቀይሯል ፡ የእኔስ ፡ ኑሮ አንተን ፡ በመከተሌ ፡ ከአንተም ፡ ጋር ፡ በመሆኔ ተጸጽቼ ፡ አላውቅም ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ በማመኔ (፭x) አዝ፦ የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አሳየኽኝ ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታ ፡ አጠገብከኝ መልካምነትህን ፡ አበዛህ ፡ በዘመኔ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ሆንክልኝ ፡ መድህኔ (፪x) ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x) የጐደለብኝ ፡ የለም ፡ ሁሉ ፡ ሞላልኝ ፡ እንጂ በረከት ፡ እንደሁ ፡ አያልቅም ፡ ከአንተ ፡ ቤት ፡ ከአንተ ፡ ደጅ የሰላም ፡ አለቃ ፡ ሆይ ፡ የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ ነህ ማንም ፡ አይመጥንህም ፡ ከምርጦች ፡ ሁሉ ፡ ልዩ ፡ ነህ (፭x) አዝ፦ የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አሳየኽኝ ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታ ፡ አጠገብከኝ መልካምነትህን ፡ አበዛህ ፡ በዘመኔ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ሆንክልኝ ፡ መድህኔ (፪x) ከሁሉ ፡ በላይ (በላይ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ከሁሉ ፡ በላይ (ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (ጌታ) (፪x) ከምን ፡ ጋር ፡ ላወዳድርህ ፡ ከማን ፡ ጋር ፡ ላስተካክልህ ከሚታይ ፡ ከማይታየው ፡ ከሁሉ ፡ ትበልጣለህ ከሁሉ ፡ ትበልጣለህ (አው ፡ ከሁሉ) ፡ ከሁሉ ፡ ትሻላለህ (ሁሁ) እድል ፡ ፈንታዬ ፡ ጌታ (እድል ፡ ፈንታዬ ፡ ጌታ) ፡ ለዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነህ (፭x) አዝ፦ የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አሳየኽኝ ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታ ፡ አጠገብከኝ መልካምነትህን ፡ አበዛህ ፡ በዘመኔ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ሆንክልኝ ፡ መድህኔ (፪x) ከሁሉ ፡ በላይ (ኦ ፡ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ጌታ ከሁሉ ፡ በላይ (ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ከሁሉ ፡ በላይ (ቃልህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (ክብርህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ መንግሥትህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ከሁሉ ፡ በላይ (ሥጋህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ጌታ ከሁሉ ፡ በላይ (ፍቅርህ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ከሁሉ ፡ በላይ (ኦ ፡ አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ) ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ከሁሉ ፡ በላይ (በላይ ፡ በላይ) (፪x)