Loading
ከጉባዔው ፡ መሃል ፡ ብዙ ፡ ሕዝብም ፡ ካለበት ተጋባዥ ፡ ሰው ፡ ሆኜ ፡ ያኔ ፡ በፍርሃት ህዝቡ ፡ ብዙ ፡ ግን ፡ ባንድ ፡ ድምፅ ፡ አቤት ፡ ዝማርያቸው መፅሐፍ ፡ ተከፍቶ ፡ ይነገራል ፡ ሰምቼ ፡ ማላውቀው (፪x) ከቃሉ ፡ የህይወት ፡ ውሃ ፡ ወደልቤ ፡ ፈሰሰ ሳላቅማማ ፡ ጠጣሁት ፡ ውስጤም ፡ ረሰረስ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ያለ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዳግመኛ ፡ ተወለድኩኝ በልቤ ፡ አምኝ ፡ በአፌም ፡ መሰከርኩኝ በዚያን ፡ ቀን ፡ አሃሃ ፡ ታሪኬ ፡ ተቀየረ በዚያን ፡ ቀን ፡ ኦሆሆ ፡ ቀንበሬ ፡ ተሰበረ በዚያን ፡ ቀን ፡ ሽክሜም ፡ ቀለለልኝ በዚያን ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አልኩኝ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ አንተን ፡ መሳይ ፡ ወዳጅ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ መሃሪ አንተን ፡ መሳይ ፡ አምላክ ለማወቅ ፡ ተከፈቱ ፡ ዓይኖቼ የመዳንን ፡ ቃል ፡ ሰምቼ ወስኜ ፡ አንተን ፡ ያገኘሁባት ያችን ፡ ቀን ፡ አልረሳት ያችን ፡ ቀን ፡ ልባርካት (፪x) ውዴ ፡ ደጁን ፡ ሲያንኳኳ ፡ በሬን ፡ ከፈትኩለት ከእኔ ፡ ጋር ፡ እራት ፡ በላ ፡ የዋህ ፡ ነው ፡ በልቡ ፡ ትሁት ተቆረሰ ፡ የሕይወት ፡ እንጀራ ፡ ዓይኖቼም ፡ ተከፈቱ እንደንቦሳ ፡ ዘለልኩኝ ፡ አይረሳኝም ፡ ዕለቱ በዚያን ፡ ቀን ፡ አሃሃ ፡ ኃጢያቴ ፡ ተሰረየ በዚያን ፡ ቀን ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ ፡ ደስታ ፡ ሆነ በዚያን ፡ ቀን ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ተቀመጥኩኝ በዚያን ፡ ቀን ፡ አምላክን ፡ እኔ ፡ ወረስኩኝ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ አንተን ፡ መሳይ ፡ ወዳጅ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ መሃሪ አንተን ፡ መሳይ ፡ አምላክ ለማወቅ ፡ ተከፈቱ ፡ ዓይኖቼ የመዳንን ፡ ቃል ፡ ሰምቼ ወስኜ ፡ አንተን ፡ ያገኘሁባት ያችን ፡ ቀን ፡ አልረሳት ያችን ፡ ቀን ፡ ልባርካት (፪x) ይገርማል ፡ እኔን ፡ መውደድህ ፡ ይገርማል ይገርማል ፡ እኔን ፡ ማሰብህ ፡ ይገርማል (፪x) ይገርማል ፡ እኔን ፡ መውደድህ ይገርማል ፡ እኔን ፡ ማሰብህ ይገርማል ፡ እኔን ፡ ማፍቀርህ ፡ ይገርማል (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.