Loading
Singer
በብዙ ፡ ነገር ፡ እንታወካለን ኑሮ ፡ ልንገፋ ፡ እንጨነቃለን በሥጋ ፡ በነፍስ ፡ እንባክናለን አርፎ ፡ መቀመጥን ከአንተም ፡ አፍ ፡ መስማትን ገና ፡ አሁን ፡ ተረዳን ፡ ሰምቶ ፡ መታዘዝን አዝ፦ ከእግርህ ፡ ሥር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው የማይጠፋም ፡ እድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x) ሲሰሙህ ፡ ደስ ፡ እንደሚልህ ፡ ጌታችን የአውራ ፡ በግ ፡ ስብ ፡ ብንሰጥህ ፡ ከእጃችን ምንም ፡ አያረካህ ፡ እንደ ፡ መስማታችን የእኛ ፡ ብቻ ፡ ይሰማ ፡ እያሉ ፡ መለፍለፍ መስማትን ፡ ያግዳል ፡ ተናግሮ ፡ አለማረፍ አዝ፦ ከእግርህ ፡ ሥር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው የማይጠፋም ፡ እድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x) ደቀ ፡ መዝሙርም ፡ ሳይሆን ፡ ከቶ ፡ ሳይማር እራሱን ፡ የሚሾም ፡ ከሹመቱ ፡ ሲሻር ብቻውን ፡ ሲወድቅ ፡ ያለ ፡ አንዳች ፡ አጋር ተግሳፅን ፡ ያገኛል ፡ ጠቢብ ፡ አስተውሎ ልማር ፡ አስቀድሜ ፡ ሩጫ ፡ ይቆይ ፡ ብሎ አዝ፦ ከእግርህ ፡ ሥር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው የማይጠፋም ፡ እድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x)