Loading
Singer
የጠላቶች ፡ ቁጣ ፡ ቢነድም ፡ በላዪ ከእነርሱ ፡ ይበልጣል ፡ አዎ ፡ የጠራኝ ፡ ጌታዬ ልቤም ፡ አይደነግጥ ፡ በወጀቡ ፡ ብዛት መንገድ ፡ ላይ ፡ አይጥለኝም ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ የታመንኩበት (፪x) ወጀቡን ፡ አይቼ ፡ ፀጋዬን ፡ አልጥልም የከበረውን ፡ ነገር ፡ አዎ ፡ ለውሾች ፡ አልሰጥም እግዚአብሔር ፡ ኃይሌ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ ፡ አይላላም በጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ እኔ ፡ ስፍራዬን ፡ አልለቅም (፪x) ከፍታዬን ፡ ልያዝ ፡ ተራራውን እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ያየልኝን አልደከምኩም ፡ ዛሬም ፡ ጉልበታም ፡ ነኝ የሰማሁት ፡ ወንጌል ፡ አላረጀም (፪x) ዮርዳኖስን ፡ አይተው ፡ እህ ፡ ሰዎች ፡ ብዙ ፡ ቢሉ እኔ ፡ እሻገራለሁ ፡ ሰምቻለሁ ፡ ቃሉን ፡ አዬ ሰምቻለሁ ፡ ቃሉን ካየልኝ ፡ በረከት ፡ እህ ፡ ከግቤ ፡ ላይ ፡ ሳልደርስ ፡ ኦሆ ወጀቡን ፡ አይቼ ፡ እኔስ ፡ አልመለስም ፡ አዬ እኔስ ፡ አልመለስም እልፍ ፡ በል ፡ ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው መንገዴን ፡ ጀምሬ ፡ እንዴት ፡ እመለሳለሁ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጣል ልቤም ፡ ላይደነግጥ ፡ ይህን ፡ ቃል ፡ አምኖታል ኧረ ፡ እንዴት ፡ ይሆናል ፡ እህ ፡ ብዬ ፡ አልጠራጠር ፡ ኦሆ እግዚአብሔር ፡ ከሰጠኝ ፡ ተራራማውን ፡ አገር አዬ ፡ ተራራማውን ፡ አገር ፈርቼ ፡ አልመለስም ፡ እህ ፡ ረጃጅሞቹን ፡ ኦሆ እገጥማቸዋለሁ ፡ ጠርቼው ፡ አምላኬን አሄ ፡ ጠርቼው ፡ አምላኬን እልፍ ፡ በል ፡ ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው መንገዴን ፡ ጀምሬ ፡ እንዴት ፡ እመለሳለሁ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጣል ልቤም ፡ ላይደነግጥ ፡ ይህን ፡ ቃል ፡ አምኖታል