Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ በድንቅ ፡ የረዳው (ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው) (፫x) ሞቷል ፡ ሲባል ፡ ሕይወት ፡ ያየ ፡ ሰዉ (ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው) (፫x) የጠላቱን ፡ ውድቀት ፡ ያየ ፡ ሰዉ (ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው) (፫x) ጌታ ፡ ከላይ ፡ ተሻገር ፡ ያለዉ (ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው) (፫x) እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ቢኮሩበት ፡ ያኮራል ስሙ ፡ ከስም ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ሲጠሩት ፡ ያስመልጣል ኮራ ፡ ብዪ ፡ እኖራለሁ ፡ ያመንኩትን ፡ አውቃለሁ ሹመቴ ፡ ሽልማቴ ፡ ከፍታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አዝ፦ ከፍታዬ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ከፍታዬ (፬x) ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ ተነሳ (እንደገና) (፫x) በእርሱ ፡ ያለፍኩትን ፡ ያን ፡ ቀን ፡ አሰበና (እንደገና) (፪x) አምልኮ ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ ተነሳ (እንደገና) (፫x) እርሱ ፡ ያደረገልኝን ፡ ዉለታ ፡ አሰበና (እንደገና) (፪x) ገና ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ገና ለአንተ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ዉለታህ ፡ አለብኝና (፪x) ዉለታ ፡ አለብኝና (፰x) ያየሁትን ፡ ሳላይ ፡ አልቀርም ፡ መንገድ ፡ ላይ እደርሳለሁ ፡ ከግቤ ፡ ህልም ፡ አለኝ ፡ ከሰማይ ሰው ፡ አይደለምና ፡ የተናገረኝ የጠራኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ቃሉን ፡ የሰጠኝ ዮሴፍ ፡ በሕይወት ፡ አለ ፡ ያውም ፡ በክብር ራዕዩን ፡ የሰጠ ፡ አለና ፡ እግዚአብሔር ሰረገላው ፡ ከደጅ ፡ ቆሟል ፡ ለማስረጃ ይሄው ፡ ዘመን ፡ መጣ ፡ ወደክብር ፡ መውጫ አዝ፦ ከፍታዬ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ከፍታዬ (፬x) ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ በልጁ ፡ ወዶኛል ልክደው ፡ የማልችለው ፡ ይህ ፡ እውነት ፡ ገብቶኛል የብረቱ ፡ መዝጊያ ፡ ምን ፡ ቢቆም ፡ ከፊቴ አውቆ ፡ ይከፈታል ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከፊቴ ንጉሥ ፡ የወርቁን ፡ ዘንግ ፡ ዘረጋልኝና ያለህግ ፡ አስገባኝ ፡ ከፋፈተውና ገና ፡ ሳልናገር ፡ ሁሉ ፡ ተሰካካ የታመንኩት ፡ አምላክ ፡ ቀድሞ ፡ ወጥቷል ፡ ለካ አዝ፦ ከፍታዬ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ከፍታዬ (፬x)