Loading
Singer
አዝ፦ ከፍ ፡ በል (፬x) በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በዝማሬ ፡ ከፍ ፡ በል በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በዝማሬ ፡ ከፍ ፡ በል ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ላልከው ለአንተ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰጣለሁ (፪x) ሥምህን ፡ ጠርቼ ፡ አላፈርኩምና ድንቅህ ፡ ለሕይወቴ ፡ ብዙ ፡ ነውና ፊትህ ፡ ወድቄ ፡ ላቅርብ ፡ ምሥጋናዬን ከፍ ፡ ከፍ ፡ ላርግህ ፡ ባለውለታዬ ከፍ ፡ በል (፬x) በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በዝማሬ ፡ ከፍ ፡ በል በምሥጋና ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በዝማሬ ፡ ከፍ ፡ በል ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ላልከው ለአንተ ፡ ምሥጋናን ፡ እሰጣለሁ (፪x) ጠላት ፡ ሊይዘኝ ፡ ከኋላዬ ፡ መጥቶ ባህሩም ፡ ሲናወጥ ፡ እስከ ፡ አፉ ፡ ሞልቶ በዘረጋሁ ፡ ጊዜ ፡ በትሬን ፡ በእምነት በድል ፡ ተሻገርኩ ፡ ሰጠመ ፡ ጠላት አምላኬ ፡ ነህ ፡ አምላኬ (፮x) አይቻለሁ ፡ ማዳንህን አይቻለሁ ፡ ጥበቃህን አይቻለሁ ፡ ችሎታህን አይቻለሁ ፡ ብርታትህን አይቻለሁ ፡ ምህረትህን አይቻለሁ ፡ ያን ፡ ፍቅርህን አይቻለሁ ፡ ጉልበትህን አይቻለሁ ፡ ስልጣንህን እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፪x) እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ እስኪ ፡ ማን ፡ አየ (፪x) ይናገር ፡ ማን ፡ አየ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አየ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x) አንተን ፡ ማን ፡ ይመስላል ፡ በዘመናት ፡ መሃል ከአንተስ ፡ ጋር ፡ እግዚአብሔር ፡ ማን ፡ ይወዳደራል የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የኃይላን ፡ ኃያል ገናናው ፡ እግዚአብሔር ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ይመስላል እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x) እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ለዘለዓለም (፪x)