Loading
አዝ፦ ውዴ ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው ከቶ ፡ ምን ፡ እርሱን ፡ ሊተካው የሕይወትን ፡ ቃል ፡ አለው ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው (፪x) መናወጥ ፡ ከሞላበት ፡ የምጥ ፡ ዘመን የእራሱ ፡ በቂ ፡ የሆነ ፡ ክፋት ፡ ያለበት ነፍሴን ፡ ከሚያስጨንቅ ፡ ዕለት ፡ ዕለት መኖሪያዬ ፡ ኢየሱስን ፡ የዘለዓለም ፡ ማለት አዝ፦ ውዴ ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው ከቶ ፡ ምን ፡ እርሱን ፡ የሚተካው የሕይወትን ፡ ቃል ፡ አለው ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው (፪x) እራሱን ፡ ሊገልጥ ፡ ወዶ ፡ ያደረገው የሕይወት ፡ መንገድ ፡ ትግል ፡ የበዛው ክፉዉን ፡ ለበጐ ፡ የለወጠው አምላኬ ፡ በጥበቡ ፡ አሳመረው አዝ፦ ውዴ ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው ከቶ ፡ ምን ፡ እርሱን ፡ የሚተካው የሕይወትን ፡ ቃል ፡ አለው ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው (፪x) በማልመርጠው ፡ መንገድ ፡ ሲማራኝ ለካስ ፡ ውዴ ፡ በሕይወት ፡ ሲጠብቀኝ ልመናዬ ፡ ዝብዘባዬ ፡ ሳያውከው መልካሙን ፡ ዘምን ፡ ለእኔ ፡ አቆየው አዝ፦ ውዴ ፡ ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው ከቶ ፡ ምን ፡ እርሱን ፡ የሚተካው የሕይወትን ፡ ቃል ፡ አለው ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ ምርጫዬ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ አምባዬ ፡ ነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.