Loading
Singer
በአንተ ፡ የተደነቀ ፡ ምህረት ፡ የበዛለት ምስግናን ፡ ያመጣል ፡ ፍቅሩን ፡ ሊገልጽበት ዘመኑን ፡ በሙሉ ፡ ቢቀኙ ፡ ለክብርህ ከመታወቅ ፡ ያልፋል ፡ የአንተስ ፡ ማንንነት ዝማሬው ፡ ቢበዛ ፡ ቢጨማምርለት ምሥጋናው ፡ ቢበዛ ፡ ቢጨማምርለት አድንቆት ፡ ቢበዛ ፡ ቢጨማምርለት የቱም ፡ አይገልጸዉ ፡ የእርሱን ፡ የእርሱን ፡ ታላቅነት የቱም ፡ አይገልጸዉ ፡ የእርሱን ፡ ኃያልነት ክቡር ፡ ነው ፡ የከበረ ፡ በክብር ፡ የተሞላ ድንቅ ፡ ነው ፡ የሚደነቅ ፡ በኃይል ፡ በሥራ (፪x) እግዚአብሔር ፡ የሚወደድ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚፈራ እግዚአብሔር ፡ የሚደነቅ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚያኮራ አምላኬ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ የቱ ፡ ዝማሬ ፡ ይገልጽሃል (፪x) ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ የቱ ፡ ምሥጋና ፡ ይገልጽሃል (፪x) አባቴ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ የቱ ፡ ምሥጋና ፡ ይገልጽሃል (፪x) ኦሆሆ ፡ አሃሃ (፬x) ላስተዋለውማ ፡ ሆሆ ፡ ፀጋው ፡ ለበዛለት ንቆ ፡ ይህን ፡ ዓለም ፡ አሃ ፡ የሚጠፋውን ፡ እውነት በእምነት ፡ እያየው ፡ ፊትህን ፡ እለት ፡ እለት ፡ ኦሆ እንዴት ፡ ደስ ፡ ያሰኛል ፡ ለክብርህ ፡ መቀኘት (፪x) ኦሆሆ ፡ አሃሃ (፬x) ክቡር ፡ ነው ፡ የከበረ ፡ በክብር ፡ የተሞላ ድንቅ ፡ ነው ፡ የሚደነቅ ፡ በኃይል ፡ በሥራ (፪x) እግዚአብሔር ፡ የሚወደድ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚፈራ እግዚአብሔር ፡ የሚደነቅ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚያኮራ