Loading
Singer
ከቶ ፡ አልደከመም ፡ ጉልበቱ ከቶም ፡ አልደነዘም ፡ ስለቱ ዛሬም ፡ አልፈዘዘም ፡ ውበቱ ይገርማል ፡ የቃልህ ፡ ጽናቱ አሁንም ፡ ይሰራል ፡ ያው ፡ ነው በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ገዢ ፡ ነው ሰማያት ፡ ቢያልፉም ፡ ምድር ቃልህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ክቡር አዝ፦ ክቡር (፫x) ፡ ቃሉ ፡ የእግዚአብሔር ክቡር (፫x) ፡ ድምጹ ፡ የእግዚአብሔር ክቡር (፫x) ፡ የእርሱ ፡ ንግግር ድምጹ ፡ ተራራውን ፡ ያቀልጣል ጠንካራውን ፡ ዝግባ ፡ ይቆርጣል ጥቅጥቅ ፡ ያለውን ፡ ጫካ ፡ ይገልጣል ጌታዬ ሆይ ድምጽህ ያስፈራል ቃልህ ፡ ሰማያትን ፡ አጽንቷል ምድርን ፡ ደግሞ ፡ መስርቷል ሕያውን ፡ ግዑዙንም ፡ ሰርቷል በዘለዓለም ፡ ክብሩ ፡ ይኖራል አዝ፦ ክቡር (፫x) ፡ ቃሉ ፡ የእግዚአብሔር ክቡር (፫x) ፡ ድምጹ ፡ የእግዚአብሔር ክቡር (፫x) ፡ የእርሱ ፡ ንግግር ወጀብ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ አውሎ ፡ ንፋሱ ሰምቶ ፡ መልስ ፡ ያልሰጠው ፡ ለድምጹ ግዑዝ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ሕያው ፡ ፍጥረት ሰምተው ፡ ማይታዘዙት በሰማያት ፡ ያሉ ፡ በምድር ይገዛሉ ፡ ለእግዚአብሔር በሁሉ ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ገናና የእኔ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነውና ከቶ ፡ አልደከመም ፡ ጉልበቱ ከቶም ፡ አልደነዘም ፡ ስለቱ ዛሬም ፡ አልፈዘዘም ፡ ውበቱ ይገርማል ፡ የቃልህ ፡ ጽናቱ አሁንም ፡ ይሰራል ፡ ያው ፡ ነው በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ገዢ ፡ ነው ሰማያት ፡ ቢያልፉም ፡ ምድርም ቃልህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ክቡር አዝ፦ ክቡር (፫x) ፡ ቃሉ ፡ የእግዚአብሔር ክቡር (፫x) ፡ ድምጹ ፡ የእግዚአብሔር ክቡር (፫x) ፡ የእርሱ ፡ ንግግር