Loading
Singer
ለቀብር ፡ ሲዘጋጅ ፡ ሰው ፡ ሬሳ ፡ ተብሎ ትንሳኤ ፡ ሲሰጠው ፡ ሕይወት ፡ ተቀጥሎ አንዳች ፡ እጣ ፡ ካሌበት ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ብቃቱ ሙታንን ፡ ላስነሳ ፡ ክብር ፡ ይሁንለቱ ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x) በባሪያዎቹ ፡ ላይ ፡ እየተገለጠ በሽታን ፡ ከሕዝቡ ፡ ደዌን ፡ ለፈወሰ ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፪x) አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ (፪x) ተዓምራትን ፡ በእጁ ፡ ሲሰራ ፡ ባይኔ ፡ አይቻለሁ አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ (፫x) ጠላቶቼን ፡ እንደገለባ ፡ ሲያቃጥላቸው በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ የክፋቱ ፡ ሸንጐ ፡ በዘንዶ ፡ ሲመራ ተገርስሶ ፡ ወድቆ ፡ ክቡር ፡ ሥም ፡ ሲጠራ ደጋግመን ፡ ሰምተናል ፡ ተቃጥለናል ፡ ሲሉ ነግቶለት ፡ ሲቦርቅ ፡ የመሸበት ፡ ሁሉ ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x) በሰማይም ፡ በምድሩ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ክብሩ ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x) በሰማይም ፡ በምድሩ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ክብሩ ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x) በሰማይም ፡ በምድሩ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ክብሩ ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x) በሰማይም ፡ በምድሩ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ክብሩ በባሪያዎቹ ፡ ላይ ፡ እየተገለጠ የቃሉን ፡ እምነት ፡ ለሕዝቡ ፡ አስተማረ ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር በባሪያዎቹ ፡ ላይ ፡ እየተገለጠ ወንጌልን ፡ ለትውልድ ፡ ለዓለም ፡ ሰበከ ክብሩ ፡ ለእግዚአብሔር ለአያሌ ፡ ዘመዓት ፡ ህመም ፡ ያሰቃዩ በባለ ፡ መድኃኒት ፡ መፍትሄ ፡ አላገኙ ደዊው ፡ ተፈወሰ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ቀምበሩ ፡ ተሰብሮ ፡ ፍፁም ፡ ነጻ ፡ ወጥቶ ሃኩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x) በሽታውን ፡ ያዳነው ፡ ሃኪሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ሃኩሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x) በሽታውን ፡ ያዳነው ፡ ሃኪሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ (፪x) ተዓምራትን ፡ በእጁ ፡ ሲሰራ ፡ ባይኔ ፡ አይቻለሁ አምነዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ (፫x) ጠላቶቼን ፡ እንደገለባ ፡ ሲያቃጥላቸው በአይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ