Loading
Singer
አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ ከዓለም ፡ ወጣሁና ፡ ምን ፡ ይቀርብኛል? ይመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ሁሉ ፡ ሞልቶልኛል በግርፋት ፡ ቁስሉ ፡ እርሱ ፡ ፈውሷታል ነፍሴም ፡ ከዚህ ፡ ውጭ ፡ ምን ፡ ያስፈልጋታል? ከዚህ ፡ የተሻለ ፡ ምን ፡ ለውጥ ፡ ሊያመጣልኝ የሚለኝ ፡ ጠላቴ ፡ ርስትህን ፡ ለውጠኝ አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ ራሴን ፡ ስመለከት ፡ ለዚህ ፡ የማልበቃ እንዴት ፡ ተደባለቁ ፡ ከአንተ ፡ ቅዱስ ፡ መንጋ? ርስትህን ፡ አወረስኸኝ ፡ ከቅዱሣን ፡ ጋራ ከአንተ ፡ ጋር ፡ አኖርኸኝ ፡ ሰማያዊ ፡ ሥፍራ ምሕረትህ ፡ ደርሶኛል ፡ ለዚህ ፡ በቅቻለሁ እኔም ፡ በዘመኔ ፡ እገዛልሃለሁ አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ ታስሬ ፡ አግኝተህ ፡ ነው ፡ አንተ ፡ ያስፈታኸኝ እኔም ፡ ነጻ ፡ ወጣሁ ፡ ጌታ ፡ ስላሰብኸኝ ስለ ፡ እኔ ፡ የሚጠይቅ ፡ አጭር ፡ መልስ ፡ ያገኛል ትዕዛዝን ፡ ሰጥተህ ፡ ነው ፡ ብለህ ፡ ያስፈልገኛል ክብርን ፡ አለበስኸኝ ፡ ውርደቴ ፡ ቀረና ተገረመ ፡ ሁሉም ፡ መዳኔን ፡ አየና አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ የማመልክህ ፡ አምላክ ፡ ጊዜያዊ ፡ አይደለም ትላንትና ፡ የሌለህ ፡ ዓለም ፡ የማታውቅህ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ ታሪክ ፡ ያፈለቀህ ለዚህች ፡ ዓለም ፡ እንኳ ፡ ራስህ ፡ መድኃኒት ፡ ነህ ለጠየቀኝ ፡ ሁሉ ፡ ለመልስ ፡ ዝግጁ ፡ ነኝ ውዴ ፡ መድኃኒቴ ፡ እኔን ፡ እንዳዳንኸኝ አዝ፦ ክብሩ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፡ መድኃኒቴ ከውስጥም ፡ ከውጭም ፡ ሰላም ፡ ሞላ ፡ ቤቴ ተመስገን ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ አንተን ፡ በማግኘቴ ፡ እኔም ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ስምህን ፡ እየጠራሁ ፡ እባርክሃለሁ ስንቱን ፡ በአንተ ፡ አልፌ ፡ ለዚህ ፡ ደርሻለሁ