Loading
ክብሬ ነህ 1- የጠላቴን ሳቅ ልትገታ ከኔ ቤት ገባህ ጌታ ከብዙ በሚሻል ፍሬ ሳሙኤልን አወጣህ ከኔ ታምነውህ እንደማታሳፍር ውርደቴን ለውጠህ በክብር አሳየህ ውድ ወዳጅነትህን ዘንበል እንድትል ሚጠና ደጅህን አዝ፡ ላመስግንህ፤ ላመስግንህ ክብሬ ኢየሱስ አንተ ነህ 2- ቢመስልም የወይን ጠጅ ውጤት መጮኼ ማንባቴ ቀን ከሌት አንደበት አልፈህ ልብ የምታይ አንተ ግን አደመጥከኝ ከላይ ዘንበል አልክ ከዙፋንህ አጠጣኸኝ ከመንፈስህ መፅናናት አይደል ሽረት ነው ለሀዘን ጭንቀቴ የሆነው የማንም እንባ ባለእዳ አይደለህም ንግግሬ ባንተ ዘንድ እንደቀልድ አይታይም ትወርድልኛለህ ሰማይን ዝቅ አድርገህ ያለቀስኩበትን/የቆዘምኩበትን ዘመኔን ልትክስ አስቀህ አዝ፡ ላመስግንህ፤ ላመስግንህ ክብሬ ኢየሱስ አንተ ነህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.