Loading
Singer
የቱን ፡ ጀምሬ ፡ የቱን ፡ ልተወው ይሄ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ያደረገውን ፡ ሳስበው ፡ ሳስበው ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው ለእኔ ፡ የሆነውን ፡ ሳስበው ፡ ሳስበው ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) አቤት ፡ በአንተ ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩኝ የጠላቴን ፡ ጉልበት ፡ ረገጥኩኝ ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል የጠላት ፡ ምሽግ ፡ ገና ፡ ይፈርሳል ክብርህን ፡ ላውራ ፡ ዛሬም ፡ ነገም የእስራኤል ፡ ቅዱስ ፡ አንተው ፡ ተባረክ ብዙ ፡ ስራዬን ፡ አንተ ፡ ሰርተሃል አመልክህ ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል (፪x) ከአንተ ፡ በአንተ ፡ በሆነው ፡ ነገር እዚህ ፡ ደረስኩ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ ደስታዬ ፡ ይኸው ፡ ፍፁም ፡ ሆነልኝ አማኑኤል ፡ ክበርልኝ የቱን ፡ ጀምሬ ፡ የቱን ፡ ልተወው ይሄ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ያደረገውን ፡ ሳስበው ፡ ሳስበው ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው ለእኔ ፡ የሆነውን ፡ ሳስበው ፡ ሳስበው ከቁጥር ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)