Loading
Singer
አዝ፦ የሰው ፡ ምኞቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ሌት ፡ ተቀን ፡ በልቡ ፡ ሚያስበው ዓይን ፡ ከማየት ፡ አይጠግብም ጆሮም ፡ ከመስማት ፡ አይሞላም እኔ ፡ ግን ፡ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጥማቴ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጉጉቴ በዚች ፡ ምድር ፡ ሳለች ፡ ሕይወቴ (፪x) ከአንተ ፡ ሚያገኘውን ፡ ፈልጐ ፡ የመጣ ከእጅህ ፡ ተቀብሎ ፡ ዳግመኛ ፡ ላይመጣ እንደልቡ ፡ መሻት ፡ ሁሉን ፡ ብትሰጠው አንተ ፡ ከሌለኸው ፡ ምንኛ ፡ ምስኪን ፡ ነው (፪x) ሰው ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል የዚህ ፡ ምድር ፡ ክብር ፡ መች ፡ ከልኩስ ፡ ያልፋል ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል አዝ፦ የሰው ፡ ምኞቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ሌት ፡ ተቀን ፡ በልቡ ፡ ሚያስበው ዓይን ፡ ከማየት ፡ አይጠግብም ጆሮም ፡ ከመስማት ፡ አይሞላም እኔ ፡ ግን ፡ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጥማቴ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው ፡ ጉጉቴ በዚች ፡ ምድር ፡ ሳለች ፡ ሕይወቴ (፪x) እንደሰው ፡ ወግ ፡ ልማድ ፡ ዓመታት ፡ ቆጥሬ ማለፍ ፡ አልፈልግም ፡ ተራ ፡ ኑሮ ፡ ኖሬ የተጠራሁለት ፡ የክብር ፡ ጥሪ ፡ ነው ማቅለል ፡ አልፈልግም ፡ እንደዋዛ ፡ ላየው ፡ እንደቀልድ ፡ ላየው ሰው ፡ ዓለሙን ፡ ቢያተርፍ ፡ ነፍሱን ፡ ግን ፡ ቢያጐድል ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል የዚህ ፡ ምድር ፡ ክብር ፡ መች ፡ ከልኩስ ፡ ያልፋል ምን ፡ ይረባዋል ፡ ምን ፡ ይጠቅመዋል ለፍቶ ፡ ያከማቸው ፡ ጐተራው ፡ ሲሞላ የማይቆርጠው ፡ ጥሙ ፡ ደግሞ ፡ ሲለው ፡ ሌላ ሲባክን ፡ ይኖራል ፡ ርጋታን ፡ ፍለጋ ከእረፍት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ ቀርቦ ፡ ሳይጠጋ