Loading
Singer
ክብራችን ፡ አንተ ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጣችን ውበታችን ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አባታችን በጨለማ ፡ ላይ ፡ የምታበራ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ አንተ ፡ ነህና ፡ ከፍ ፡ በል የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ሞትን ፡ ገዳይ የዳዊት ፡ ዘር ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ኤልሻዳይ ሲኦልን ፡ ድል ፡ ነስተህ ፡ ቀንበር ፡ ሰባሪ ዘራችን ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ዘማሪ :ከፍ በል የአንተ ፡ በመሆኔ ፡ ኮራሁኝ ፡ እኔ የእኔ ፡ ነህ ፡ ሲለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ አለኝ (፪x) አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) ፡ በምድር ፡ ላይ (ሆ) የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ጥግ ፡ የበላይ ሁሉም ፡ ገደብ ፡ ልክ ፡ አለው የእኔ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው አቻ ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ወደር ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ምድር ፡ አልቻለችም ፡ አለቃዋን ፡ ይዛ መልሳ ፡ ተፋችው ፡ ፈጣሪዋን ፡ ታዛ ዓለምና ፡ ሰይጣን ፡ ሲዖል ፡ ያልቻለው የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አቻ ፡ የሌለው አቻ ፡ የሌለው ፡ ወደር ፡ የሌለው ኢየሱስዬ ፡ ብቻ ፡ ሞት ፡ ያልበገረው አቻ ፡ የሌለው ፡ ወደር ፡ የሌለው (፪x) አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) ፡ በምድር ፡ ላይ (ሆ) የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ጥግ ፡ የበላይ ሁሉም ፡ ገደብ ፡ ልክ ፡ አለው የእኔ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው አቻ ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ወደር ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እግሩ ፡ እንደ ፡ ጋለ ፡ ናስ ፡ ዐይኖቹ ፡ ነበልባል ፡ ነው እርሱን ፡ ተመልክቶ ፡ የሚቆም ፡ ሰው ፡ ማነው ስንቱ ፡ ጀግና ፡ ሞቶ ፡ መቃብር ፡ ሲቀር ኢየሱስ ፡ ተነስቷል ፡ አርጓል ፡ በክብር ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ነው ፡ ያለ ፡ የነበረ ወደፊትም ፡ ይኖራል ፡ ገና ፡ እየከበረ እየተከበረ ፡ ገና ፡ እየከበረ (፪x) ክብራችን ፡ አንተ ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጣችን ውበታችን ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አባታችን በጨለማ ፡ ላይ ፡ የምታበራ የንጋት ፡ ኮከብ ፡ አንተ ፡ ነህና ፡ ከፍ ፡ በል የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ሞትን ፡ ገዳይ የዳዊት ፡ ዘር ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ኤልሻዳይ ሲኦልን ፡ ድል ፡ ነስተህ ፡ ቀንበር ፡ ሰባሪ ዘራችን ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ዘማሪ : ከፍ:በል የአንተ ፡ በመሆኔ ፡ ኮራሁኝ ፡ እኔ የእኔ ፡ ነህ ፡ ሲለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ አለኝ (፪x) አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) ፡ በምድር ፡ ላይ (ሆ) የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ጥግ ፡ የበላይ ሁሉም ፡ ገደብ ፡ ልክ ፡ አለው የእኔ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው አቻ ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ወደር ፡ የሌለው (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዢ ፡ ሲፎክር ፡ ሲያቅራራ ገደልኩት ፡ ቀበርኩት ፡ እያለ ፡ ሲያወራ በትንሳኤው ፡ ጉልበት ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ጠላቴም ፡ ወደቀ ፡ በይሁዳ ፡ አንበሳ ሰባቱን ፡ ማህተም ፡ ቋጠሮን ፡ የፈታ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ (፫x) የይሁዳ ፡ አንበሳ ፣ የይሁድ ፡ አንበሳ (፪x) ለክብሩ (ሆ) ፡ ለኃይሉ (ሆ) ቢዘመር (ሆ) ፡ ለስሙ (ሆ) ቢወራ ፡ በምድር ፡ አይበቃም ፡ ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር (፫x) ፡ አለኝ ፡ ዘምር ለእግዚአብሔር (፫x) ፡ አለኝ ፡ ዘምር "ሃሌሉያ ፡ እሰይ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ አቻ ፡ የለውም"