Loading
Singer
ከእንግዲህ ፡ ለማን ፡ ብዬ ፡ ለምን ፡ ብዬ አልሳሳም ፡ ለሕይወቴ ፡ ተስገብግቤ ለእኔ ፡ ሕይወት ፡ ክርስቶስ ፡ እንደሆነ ፡ አውቃለሁ እራሴንም ፡ እንደመስዋዕት ፡ ፉቱ ፡ አቀርባለሁ (፪x) ለእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ (ለእግዚአብሔር ፡ ነው) ለእኔ ፡ ሕይወት ፡ የማይቆጨኝ (የማይቆጨኝ) ፡ ብሰዋለት ለእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ (ለእግዚአብሔር ፡ ነው) ለእኔ ፡ ሕይወት ፡ የማይቆጨኝ ፡ ብሰዋለት ዓይኖቼ ፡ በርተውልኝ ፡ ጌታን ፡ ሳየው ቸርነቱን ፡ ቀምሼ ፡ ሳጣጥመው ሌላው ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ይደበዝዝና እርሱ ፡ ብቻ ፡ ይሆናል ፡ ልቤን ፡ የሚሞላ (፪x) ክብሩን ፡ ሳየው ፡ (ክብሩን ፡ ሳየው) ግርማውን ፡ ያስጥለኛል ፡ (ያስጥለኛል) ፡ ሁሉንም ክብሩን ፡ ሳየው ፡ (ክብሩን ፡ ሳየው) ግርማውን ፡ ያስጥለኛል ፡ ሁሉንም ክብሩን ፡ ሳይሆን ፡ ሞቱን ፡ የተመኙ የሄደበትን ፡ መንገድ ፡ ተረድተውት ማቄን ፡ ጨርቄን ፡ ሳይሉ ፡ ሁሉንም ፡ ወርውረው እርሱን ፡ እርሱን ፡ ያሉት ፡ ከቶ ፡ ለምንድን ፡ ነው (፪x) ያ ፡ ፍቅሩ ፡ ነው ፡ (ያ ፡ ፍቅሩ ፡ ነው) የሚያስጥለው ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ (ሌላ ፡ ነገር) ፡ የማያስመኘው ፡ ነው ሊያፈቅሩ ፡ ነው ፡ (ሊያፈቅሩ ፡ ነው) የሚያስጥለው ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ (ሌላ ፡ ነገር) ፡ አያስመኝም ለእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ (ለእግዚአብሔር ፡ ነው) ለእኔ ፡ ሕይወት ፡ የማይቆጨኝ ፡ (የማይቆጨኝ) ፡ ብሰዋለት ክብሩን ፡ ሳየው ፡ ግርማውን ያስጥለኛል ፡ (ያስጥለኛል) ፡ ሁሉንም