Loading
Singer
ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን ሰማይ ፡ ዝፋንህ ፡ ነው ፡ መቀመጫህ ምድርም ፡ ለእግሮችህ ፡ መርገጫህ ለትልቅነትህ ፡ ወሰን ፡ ነህ ፡ የሌለህ ሰማያትንም ፡ በስንዝር ፡ የለካህ እንሰግዳለን ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ጌታ ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን እስትንፋሽን ፡ ለሙታን ፡ ትሠጣለህ በባዶ ፡ ሸለቆ ፡ ውሃን ፡ ትሞላለህ ጥበብህን ፡ ችሎታህን ፡ ማን ፡ ይለካዋል ያልነበርን ፡ እንደምታኖር ፡ አውቀዋል ከፍ ፡ ያልከው ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን እንዲበላ ፡ እንዲጠጣ ፡ ለራሱ ፡ እንዲኖር ብቻ ፡ አልነበርም ፡ ሰውን ፡ በእጅህ ፡ መስራት እንዲያመልክህ ፡ በታላቅነት ፡ እንዲያከብርህ መሆኑን ፡ ተረድቻለሁ ፡ እኔን ፡ መፍጠርህ ታላቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ ልባችንን ፡ ከእጃችን ፡ ጋር በሰማይ ፡ ወዳለው ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር እናነሳለን ፡ ክብርንም ፡ እንሰጣለን እናመልካለን ፡ በፊቱ ፡ እንሰግዳለን