Loading
የድሃን ፡ ማድጋ ፡ ዘይት ፡ የሚሞላው ከችግር ፡ አውጥቶ ፡ በደስታ ፡ ሚያኖረው ለአንድ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ ለብዙ ፡ ይተርፋል ክበር ፡ እንበለው ፡ ይገባዋል አዝ:- ክበር ፡ ክበርልን ፡ ክበር ፡ እንበለው መክበር ፡ የሚገባው ፡ ቸር ፡ አምላክ ፡ ነው ለቅሶን ፡ ወደ ፡ ደስታ ፡ ወደ ፡ ሳቅ ፡ ለውጧል ኢየሱስ ፡ ሊመሰገን ፡ ይገባዋል በሽባነት ፡ ታስሮ ፡ እንድሜውን ፡ ለፈጀው ወዳጅ ፡ ዘመድ ፡ ትቶት ፡ ተስፋ ፡ ለቆረጠው ታምረኛው ፡ ኢየሱስ ፡ በጊዜው ፡ ይደርሳል እስራቱን ፡ ፈቶ ፡ ያዘልላል አዝ:- ክበር ፡ ክበርልን ፡ ክበር ፡ እንበለው መክበር ፡ የሚገባው ፡ ቸር ፡ አምላክ ፡ ነው ለቅሶን ፡ ወደ ፡ ደስታ ፡ ወደ ፡ ሳቅ ፡ ለውጧል ኢየሱስ ፡ ሊመሰገን ፡ ይገባዋል ሙቱን ፡ ከመቃብር ፡ ተጣርቶ ፡ ያስነሳል በቃ ፡ የተባለውን ፡ ነፍስ ፡ ይዘራበታል ለእርሱ ፡ ማይታዘዝ ፡ ምን ፡ አለ ፡ በውኑ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ይንገሥ ፡ በዙፋኑ አዝ:- ክበር ፡ ክበርልን ፡ ክበር ፡ እንበለው መክበር ፡ የሚገባው ፡ ቸር ፡ አምላክ ፡ ነው ለቅሶን ፡ ወደ ፡ ደስታ ፡ ወደ ፡ ሳቅ ፡ ለውጧል ኢየሱስ ፡ ሊመሰገን ፡ ይገባዋል
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.