Loading
Singer
፡ ፡ :አዝ፦ ክብርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም ንገሥልኝ ፡ ብዬ ፡ በልቤ ፡ አልረካሁም ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምትወደው ባቀርብልህ ፡ ጌታ ፡ ምንም ፡ ባልሰለቸው ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ከሚያከብሩህ እኔን ፡ ከመደብከኝ ፡ ከሚያመሰግኑህ ጥማቴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ አክብርሀለሁ በቀንም ፡ በሌሊትም ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ ፡ :አዝ፦ ክበርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም ሰማይና ፡ ምድር ፡ ክብርህን ፡ ያወራሉ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እያሉ እኔም ፡ ክብርህን ፡ ላውራ ፡ ለትውልድ ፡ ልናገር የሚመስልህ ፡ የለም ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ፡ :አዝ፦ ክበርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም ፊትህን ፡ ወደኔ ፡ መልሰሃልና የአንተ ፡ ወገን ፡ አርገህ ፡ ዋጅተኸኛልና ከምርጦችህ ፡ ጋራ ፡ እኔም ፡ ተስማምቸ እስግድልሃለሁ ፡ መቅደስህ ፡ ገብቸ ፡ ፡ :አዝ፦ ክበርልን ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም የምለው ፡ ብዙ ፡ አለኝ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ የማወራው አምላኬ ፡ ይሔ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የምናገረው የሚሰማኝና ፡ የሚያየኝ ፡ ያክብርህ የኔ ፡ ብቻ ፡ አይበቃም ፡ ዘሬም ፡ ይገዛልህ ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው