Loading
Singer
ዐይኔ ፡ በማየቱ ፡ አንተን ፡ ያደንቅሃል ጆሮዬ ፡ በመስማቱ ፡ ከፍ ፡ ያደርግሃል ነፍስ ፡ መንፈስ ፡ ሥጋዬ ፡ አንተን ፡ ሾመውሃል ተስማምተው ፡ ኢየሱስ ፡ ይግዛን ፡ ብለውሃል አዝ፦ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር (፪x) ፡ እግዚአብሔር ክበር ፡ ተመስገን ፡ ንገሥ (፪x) ፡ ጌታ ፡ እየሱስ አበቦች ፡ ፈንድቁ ፡ እንሰሶች ፡ ዝለሉ ዛፎች ፡ አሸብሽቡ ፡ አእዋፍ ፡ ዘምሩ አዲስ ፡ ምሥጋና ፡ አምጡ ፡ አሜን ፡ ዕልል ፡ በሉ በፊቱ ፡ ስገዱ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ አዝ፦ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር (፪x) ፡ እግዚአብሔር ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር ፡ ንገሥ ፡ መስፈስ ፡ ቅዱስ ከበሮው ፡ ይመታ ፡ በገናው ፡ ይደርደር መለከት ፡ ይነፋ ፡ እምቢልታው ፡ ይጨመር ክራሩንም ፡ ቃኙት ፡ አዲስ ፡ ቅኔ ፡ መዝሙር በእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና ፡ ይሙላ ፡ ሰማይ ፡ ምድር አዝ፦ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር (፪x) ፡ እግዚአብሔር ክበር ፡ ተመስገን ፡ ንገሥ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፏፏቴዎች ፡ ፈንጩ ፡ በአምላካችሁ ፡ ፊት ጨረቃ ፡ ድመቂ ፡ ፍኩ ፡ ከዋክብት ብቻውን ፡ ታምራት ፡ ድንቅ ፡ አድርጓልና ዙፋኑን ፡ ይክበበው ፡ ክብርና ፡ ምሥጋና አዝ፦ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ክበር (፪x) ፡ እግዚአብሔር ክበር ፡ ተመስገን ፡ ንገሥ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ንገሥ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ