Loading
Singer
አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ ውዳሴና ፡ ዕልልታ አምልኮና ፡ ስግደት ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x) ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x) መላዕክት በሠማይ ፡ ያሉ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እያሉ ቀን ፡ የላቸው ፡ ሌሊት ፡ ሁልጊዜ ፡ የሚያከብሩት ዘለዓለማዊ ፡ ንጉሥ ፡ ኃያል ፡ የክብር ፡ ጌታ መጽሐፉን ፡ የከፈተ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ ውዳሴና ፡ ዕልልታ አምልኮና ፡ ስግደት ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x) ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x) የወደቁ ፡ መላዕክት ፡ አጋንንት ፡ በጥልቅ ፡ ያሉ ስሙ ፡ ሲጠራባቸው ፡ ሁሌ ፡ ይንቀጠቀጣሉ ተራሮች ፡ ሚጤሱለት ፡ ኮረብቶች ፡ ሚዘሉለት ጌታ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ የጽዮኑ ፡ ዓለም አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ ውዳሴና ፡ ዕልልታ አምልኮና ፡ ስግደት ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x) ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x) በፍጥረት ፡ መጀመሪያ ፡ ከሙታንም ፡ በኩር ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ የሆነ ፡ ኢየሱስ ፡ ቃለ ፡ እግዚአብሔር ፀጋ ፡ እውነትን ፡ ተሞልቶ ፡ በእኛ ፡ ዘንድ ፡ ያደረ ክርስቶስ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ያለና ፡ የነበረ አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ ውዳሴና ፡ ዕልልታ አምልኮና ፡ ስግደት ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x) ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x) ከዘር ፡ ከነገድ ፡ ሁሉ ፡ ከአገር ፡ ከወገን እኛን ፡ በደሙ ፡ አጭቶ ፡ ካህናት ፡ ያደረገን መንፈሱን ፡ ያፈሰሰ ፡ ፀጋውን ፡ የሰጠን የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን አዝ፦ ክብር ፡ ለክብር ፡ ጌታ ውዳሴና ፡ ዕልልታ አምልኮና ፡ ስግደት ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፪x) ኢየሱስ ፡ ይሁንለት (፬x)