Loading
Singer
ጠዋት ፡ ሳልል ፡ ማታ ፡ አቀርባለሁ ፡ ምሥጋና (፪x) ጠዋት ፡ ሳልል ፡ ማታ ፡ እሰዋለሁ ፡ ምሥጋና (፪x) ዕለቱን ፡ ሙሉ ፡ ክበር ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አይበቃኝም እንዲሁማ ፡ በቀላሉ ፡ አይወጣልኝም ዕለቱን ፡ ሙሉ ፡ ንገሥ ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አይበቃኝም እንዲሁማ ፡ በቀላሉ ፡ አይወጣልኝም ክበር ፡ ብዬ ፡ ሳልጨርስ ፡ ይመሽብኛል ፡ ይመሽብኛል ንገሥ ፡ ብዬ ፡ ሳልጨርስ ፡ ይነጋብኛል ፡ ይነጋብኛል (፪x) ዕለቱን ፡ ሙሉ ፡ ክበር ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አይበቃኝም እንዲሁማ ፡ በቀላሉ ፡ አይወጣልኝም ዕለቱን ፡ ሙሉ ፡ ንገስ ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አይበቃኝም እንዲሁማ ፡ በቀላሉ ፡ አይወጣልኝም ጌታ ፡ ተብሎ ፡ ምን ፡ ይቀጠላል (፪x) የምጋሥና ፡ ቃል ፡ ሁሉም ፡ አንሶሃል (፪x) አምላክ ፡ ተብሎ ፡ ምን ፡ ይቀጠላል (፪x) የዝማሬ ፡ ቃል ፡ ሁሉም ፡ አንሶሃል (፪x) አንተን ፡ ማምለኪያ (፪x) እስከዛሬም ፡ አንሷል ፡ ቢጨመርም ፡ ያንሳል እድሜ ፡ ልክም ፡ ያንልሳል ፡ ዘላለምም ፡ ያንሳል (፪x) ግን ፡ ያለኝን ፡ አልቆጥብም ያንሳል ፡ ብዬ ፡ አላቆምም (፪x) ዳር ፡ ዳር ፡ አልልም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን አገባለሁ ፡ ምስጋናው ፡ መሃል (፪x) ዳር ፡ ዳር ፡ አልልም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን አገባለሁ ፡ አምልኮ ፡ መሃል ፡ እገባለሁ ፡ ዝማሬው ፡ መሃል ማልችለው ፡ አለማምለክ ፡ ነው ፡ ምያቅተኝ ፡ አለማምለክ ፡ ነው አምልኮ ፡ አውቅበታለሁ ፡ እንዲያውም ፡ አሳምራለሁ (፪x) እኔ ፡ ምያቅተኝ ፡ እኔ ፡ የማልችለው አለማመስገን ፡ አለማምለክ ፡ ነው (፪x) ጌታ (፲፪x) ክብር ፡ ለአንተ ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይሰጣል (፪x) ክበር ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይገባል (፪x) ከትላንት ፡ ይልቅ ፡ ዛሬ ፡ አንተን ፡ ላከብር ተነሳስቻለሁ ፡ ተነሳስቻለሁ (፪x) ክብር ፡ ለአንተ ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይሰጣል (፪x) ክበር ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይገባል (፪x) የአንተን ፡ ምሥጋና ፡ ለማንም ፡ አልሰዋም (፪x) የአንተን ፡ ክብር ፡ ለማንም ፡ አልስጠም (፪x)