Loading
Singer
፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ጌታ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ በሰማይ ፡ በምድር መካኒቱን ፡ በልጅ ፡ የባረካት ደስ ፡ የተሰኘች ፡ ሴት ፡ ያደረካት ምስኪኑን ፡ ከአመድ ፡ ያነሳኸው ለሹመት ፡ ሽልማት ፡ ያበቃኸው ፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ባሕሩን ፡ ለሁለት ፡ የከፈልከው ሾላውን ፡ ከስሩ ፡ የነቀልከው ለደካማው ፡ ኃይልን ፡ የሰጠኸው በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ ያራመድከው ፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር ዘንዶውን ፡ የወጋህ ፡ የቆራረጥክ ጠንካራውን ፡ አለት ፡ የሰነጠክ የተራበችውን ፡ ነፍስ ፡ ያጠገብክ የተበተኑትን ፡ የሰበስብክ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር የእስረኞችን ፡ ጩኸት ፡ አዳምጠሃል የወህኒውን ፡ መዝጊያ ፡ ሰባብረሃል ሰው ፡ የረሳቸውን ፡ አስታውሰሃል ያልጋ ፡ ቁራኞችን ፡ ፈውሰሃል ክብር ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ፡ :አዝ፦ ክብር ፡ ክብር ፡ ክብር