Loading
Singer
ለናዝሬት ፡ ኢየሱስ ፡ እንደበግ ፡ ለታረደው በደሙ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ሰዎችን ፡ ለዋጀው ለአምላክ ፡ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ላደረገው ፡ በረከትና ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ያለና ፡ የነበር ፡ የሚመጣው ፡ ሁሉን ፡ የሚገዛው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አእላፋት ፡ መላእክት ፡ ያከብሩታል ፡ ተመስገን ፡ እያሉ ፡ ይሰግዱለታል ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ የምሥጋናችን ፡ ቀን መርገምን ፡ አርቆዋል ፡ ሰርታል ፡ ስራችንን በፍፁም ፡ ፈቃዱ ፡ እንዲሁ ፡ አድኖናል ስገድትም ፡ ምሥጋናም ፡ ለእርሱ ፡ ያንስበታል ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ መጀመሪያው ፡ የሁሉ ፡ ፍጻሜ ፡ መጨረሻው የሚመጣው ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የዓለምን ፡ ሃጥያት ፡ ያስወገደው ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ባባቱ ፡ ቀኝ ፡ ላለው ፡ ለጌታ ፡ ለኢየሱስ ፡ አምልኮ ፡ ዝማሬ ፡ ከልባችን ፡ ይፍሰስ በክብር ፡ ታጅቦ ፡ በደመና ፡ ይመጣል ፡ ያለም ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ለክብሩ ፡ ይሰግዳል ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው ፡ ክብር ፡ እንስጠው ፡ ይገባዋል ፡ ስግደት ፡ እናክብረው በምሥጋና ፡ ዜማ ፡ በዕልልታ ፡ በፊቱ ፡ እንዘምር ፡ በደስታ ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡