Loading
Singer
እነዚያስ ፡ ያንን ፡ የተማመኑበት ተሰነካከለ ፡ ተስፋ ፡ ያደረጉበት ክብራቸው ፡ ወደቀ ፡ ቀንዳቸው ፡ ተመታ በዙፋኑ ፡ ከብሮ ፡ አለ ፡የእኛ ፡ ጌታ ብቻህን ፡ ተዐምራት ፡ ያደረግህ ፡ ጌታ ፍፁም ፡ የማትረታ አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ ሠማይን ፡ እንደ ፡ መጋረጃ ፡ ዘርግቶ እልፍኙን ፡ በውኃ አሳምሮ ፡ ሰርቶ ምንም ፡ የሌለበት ፡ እጅግ ፡ ከደረቀ አለቱን ፡ ሰንጥቆ ፡ ውሃን ፡ አፈለቀ (፪x) አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ ሸለቆን ፡ የሚሞላ ፡ ተራራን ፡ የሚንድ አገልጋዩን ፡ እንደ ፡ ነበልባል ፡ የሚያነድ በተራሮች ፡ ላይ ፡ ውሆችን ፡ የሚያቆም እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ የለም አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ በሚንበለበለው ፡ እሳት ፡ ውስጥ ፡ ቢከተን የምታምኑት ፡ አምላክ ፡ ያድናችሁ ፡ ቢለን የምናምነው ፡ አምላክ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ አያየን ነጥቆ ፡ ያወጣናል ፡ ከእሳቱ ፡ ወላፈን (፪x) አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ መዝገቡም ፡ ይከፈት ፡ ታሪክም ፡ ይመርመር አንደበትም ፡ ያውራ ፡ መስካሪም ፡ ይመስክር ብርቱ ፡ የሆነ ፡ አምላክ ፡ ማነው ፡ ከአንተ ፡ በቀር የሚነደውን ፡ እሳት ፡ በእሳት ፡ የሚሽር (፪x) አዝ፦ በሠማይ ፡ በምድር ፡ ከቶ ፡ የለህ ፡ አቻ ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ንገሥ ፡ አንተ ፡ ብቻ