Loading
Singer
ኃያላን ፡ ከምድር ፡ ተሰብረው ፡ ሲወድቁ በራሳችው ፡ በትር ፡ እራሳቸው ፡ ሲያልቁ አንዱ ፡ አንዱን ፡ ሲተካው ፡ ዓለም ፡ ሲለዋወጥ የጀግና ፡ ሰው ፡ ዙፋን ፡ መንበር ፡ ሲገለበጥ አንተን ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሊደፍር ፡ ማን ፡ ቻለ ሥምህ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እጅጉን ፡ አየለ ብንሰግድልህስ ፡ አቤት ፡ ያንስብሃል ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክብርህን ፡ በዓይናችን ፡ አይተናል አዝ፦ ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ (፫x) (ይገባሃል) ፡ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x) ፈርዖን ፡ ሊያጠፋን ፡ ኃይሉን ፡ አዘጋጀ እንዲያው ፡ ላይሆንለት ፡ ብዙ ፡ ጦሩን ፡ ፈጀ አንተ ፡ ግን ፡ በድንገት ፡ ደርሰህ ፡ ድል ፡ አረከው ክብር ፡ የሚገባው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ ነው ዙፋንህ ፡ የፀና ፡ ሥምህ ፡ የገነነ ማን ፡ አለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የተመሰገነ ብንሰግድልህስ ፡ አቤት ፡ ያንስብሃል ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክብርህን ፡ በዓይናችን ፡ አይተናል አዝ፦ ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ (፫x) (ይገባሃል) ፡ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x) ሥምህን ፡ ሊያጠፉት ፡ ብዙዎች ፡ ተነሱ ያለ ፡ የሌለውን ፡ ጦሩን ፡ አስገዝተው ሽር ፡ ጉድ ፡ ሲሉ ፡ በምድር ፡ ጥበብ ፡ ዕውቀት አንተ ፡ በሰራኸው ፡ ታይተው ፡ ሊነግሱበት አስበው ፡ ሲጥሩ ፡ ከላይ ፡ አየህና ክብርህስ ፡ ሲነካ ፡ መቼ ፡ ትውድና ክንድህን ፡ ዘርግተህ ፡ ገለባበጥካቸው እንደ ፡ ምድር ፡ ትቢያ ፡ በነነ ፡ ሥማቸው አዝ፦ ክበር ፡ አንተ ፡ ብቻ (፫x) (ይገባሃል) ፡ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና ፣ ይገባሃልና (፪x)