Loading
Singer
አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልኑር ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ኢየሱስ ፡ ልኑር ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ያለ ፡ አንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ብቻዬን ፡ አያምርብኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር (፪x) በንጉሥ ፡ ጮማ ፡ ከኖሩ ፡ ቆሎ ፡ ቆርጥመው ፡ ያደሩ አስር ፡ እጅ ፡ አማረባቸው ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ የወገኑ በምድር ፡ ተጨምጭቦልኝ ፡ በሰማይ ፡ ከምታፍርብኝ ይቅርብኝ ፡ ሁሉም ፡ ይቅር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ብቻ ፡ ልኑር መራብን ፡ አውቃለሁ ፡ መጥገብን ማግኘትን ፡ አውቃለሁ ፡ ማጣትን እኔ ፡ ማይሆንልኝ ፡ ማያምርብኝ ያላንተ ፡ መኖር ፡ ነው ፡ የታውቅክልኝ ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር (፪x) አዝ፦ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልኑር ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ኢየሱስ ፡ ልኑር ፡ አንተ ፡ ጋር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ያለ ፡ አንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ብቻዬን ፡ አያምርብኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ባልጠጣ ፡ ያረካኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋር ቢቃጠል ፡ ወጣትነቴ ፡ ቢነድም ፡ ለአንተ ፡ ጉልበቴ ቢቀናም ፡ ክፉ ፡ ጠላቴ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አባቴ የሰው ፡ ልጅ ፡ ዕድሜ ፡ ሰንቃላ ፡ ሰማንያ ፡ አመት ፡ የማይሞላ ድካም ፡ ነው ፡ ከዚያ ፡ በኋላ ፡ አልሆንም ፡ እኔስ ፡ ተላላ ሺህ ፡ ዓመት ፡ አልኖርም ፡ በምድር እንደእንፋሎት ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ ዘመን በቃ ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ልኑርና ዘመኔን ፡ ጨርሰው ፡ ጌታ ፡ ቀድስና ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር (፪x) ሙሴ ፡ አይቶ ፡ ብድራቱን ፡ የልጅ ፡ ልጅ ፡ ንግስናውን ንቆታል ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ብሎ ፡ አልጋውን ፡ ክብሩን ፡ ተምኖ ኧረ ፡ ለእኔ ፡ ትልቅ ፡ እድል ፡ ነው ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ብዬ ፡ ምኖረው እንኳን ፡ አገልጋይ ፡ ሆኜ ፡ ይበቃል ፡ ባሪያ ፡ መባሌ የእኔ ፡ መጨረሻ ፡ ጥግ ፡ እርካታዬ መገኘትህ ፡ ሲኖር ፡ በቤት ፡ በጓዳዬ ያን ፡ ጊዜ ፡ በፍፁም ፡ ልቤ ፡ ኧረካለሁ ፊትህን ፡ እያየሁ ፡ ሁልጊዜ ፡ እጠግባለሁ ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ባልበላ ፡ እጠግባለሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ይሄ ፡ ልቤ ፡ ተመኝቶሃል ፡ ልኑር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ባልጠጣ ፡ ያረካኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋር