Loading
Singer
ሰማይ ፡ ሆነ ፡ ምድር ፡ ጌታ ፡ ሆኖ ፡ የሚመለከው ስግደት ፡ የተገባው ፡ . (1) . ፡ ያለኸው ዓይናችን ፡ በራልን ፡ ማን ፡ አዳኝ ፡ እንደሆነ ፡ አየን ስምህ ፡ ክብራችን ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ነን ፡ አንኮራለን እውነተኛው ፡ አምላክ ፡ ለህዝቦችህ ፡ ያለህ አዝ:- ከአንተ ፡ በላይ ፡ አምላክ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በላይ (፰x) ስንቱን ፡ ደፋርና ፡ ትዕቢተኛን ፡ ጥለሃል በውጊያ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ ቁጣህም ፡ ታይቶልሃል ሞኛሞኞች ፡ ሆነው ፡ ሊጣሉህ ፡ መጡ ፡ ታጥቀው የውርደት ፡ አቧራ ፡ ከደናቸው ፡ . (2) . ጀግና ፡ ነው ፡ አርሱ ፡ አሉ ፡ . (3) . ፡ ጌታቸው አዝ:- ከአንተ ፡ በላይ ፡ ጀግና ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በላይ (፰x) ወልደህ ፡ እንደሰው ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ አትጥልም እንጀራም ፡ እያለ ፡ ድንጋይ ፡ ብላ ፡ አትልም የወላጅ ፡ አንጀትህ ፡ ይንሰፈሰፍልናል ብሩካን ፡ እጆችህ ፡ ቆርሰው ፡ ይመግቡናል እንደአንተ ፡ ያለ ፡ አባት ፡ የትስ ፡ ይገኝልናል አዝ:- ከአንተ ፡ በላይ ፡ አባት ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በላይ (፰x) ለበሽታ ፡ ሁሉ ፡ ፍቱን ፡ መድሃኒት ፡ አለህ ሞት ፡ አፋፍ ፡ ላይ ፡ ላሉ ፡ ብቸኛ ፡ መልስ ፡ አንተ ፡ ነህ በእጆችህ ፡ ተዳሰው ፡ አፎይ ፡ ያሉ ፡ ብዙ ፡ አሉ ሌት ፡ ተቀን ፡ ከማልቀስ ፡ ክእንባ ፡ የተገላገሉ ይኸው ፡ ተፈውሰው ፡ ለክብርህ ፡ ይዘምራሉ አዝ:- ከአንተ ፡ በላይ ፡ ፈዋሽ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በላይ (፰x) "ሃሌሉያ ፡ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቢሆን እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ጌታ ፡ ሆይ ከምድር ፡ ጫፍ ፡ እስከምድር ፡ ጫፍ ታላቁ ፡ ሥምህ ፡ የተባረከ ፡ ይሁን" ሃሌሉያ(፲፮x)