Loading
Singer
ከአፌ ፡ የማይጠፋ ፡ የማልረሳው ፡ የማልረሳው ከአፌ ፡ የማይጠፋው ፡ የማልተወው ፡ የማልተወው ከየት ፡ እንዳነሳኝ ፡ ነው (፬x) አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ለጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና (፪x) በሕይወት ፡ ለመኖር ፡ የሚያስችለኝ ከሠማይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ወጥቶልኝ ነው ፡ እንጂ ፡ በቤቱ ፡ መሠንበቴ መቼ ፡ በኃይልና ፡ በብርታቴ ፡ አሃ ፡ በብርታቴ እርሱ ፡ ነው ፡ ከደሜ ፡ ያጠራኝ አፍረቴን ፡ ሸፍኖ ፡ ያነሳኝ እርቃኔን ፡ በመጎናጸፍያው ፡ ደብቆ ፡ ያከበረኝ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ አሃ ፡ እርሱ ፡ ነው ስለዚህ ፡ ጎትጓች ፡ አልፈልግም ፡ አምላኬን ፡ ለማመስገን ፡ ጌታዬን ፡ ለማመስገን በእርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የተሻገርኩት ፡ ያለፍኩት ፡ ያንን ፡ ክፉ ፡ ቀን (፪x) አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ለጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና (፪x) በንጉሥ ፡ ገበታ ፡ ተቀምጬ ፡ ከሕይወት ፡ እንጀራው ፡ እንድበላ ንጉሥ ፡ ለሚወደው ፡ እንዲህ ፡ ይሁን ፡ ተብሎ ፡ ሲነገር ፡ ሲወራ (፪x) በትልቁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ተወድጄ ፡ ከውዳቂ ፡ ስፍራ ፡ ተነስቼ በፊቱ ፡ ልቆም ፡ ዘንድ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ እስከዚህ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ የወደደኝ ፡ አሃሃ ፡ የወደደኝ ስለዚህ ፡ ጎትጓች ፡ አልፈልግም ፡ አምላኬን ፡ ለማመስገን ፡ ጌታዬን ፡ ለማመስገን በእርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የተሻገርኩት ፡ ያለፍኩት ፡ ያንን ፡ ክፉ ፡ ቀን (፪x) ከአፌ ፡ የማይጠፋ ፡ የማልረሳው ፡ የማልረሳው ከአፌ ፡ የማይጠፋው ፡ የማልተወው ፡ የማልተወው ከየት ፡ እንዳነሳኝ ፡ ነው (፬x) አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ለጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እንደገና (፪x)