Loading
Singer
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ከአፌ ፡ አላወርድም ፡ ይህን ፡ ሥስምክን አላርፍም ፡ አልረካም ፡ እስካገኝህ (፪x) ውኃ በማጣት ፡ እንደደረቀ ፡ መሬት አግኝታ ፡ እስክትረካ ፡ ነፍሴ ፡ እያት ፡ ስትዋትት ሃይልና ፡ ሞገስህ ፡ በሞላው ፡ መቅደስህ ፍቀድልኝና ፡ ልየው ፡ ያን ፡ ፊትህን እንጨትና ፡ ውኃ ፡ በሌለበት ፡ ቦታ እኔ ፡ ግን ፡ እሄዳለሁ ፡ ውድዬን ፡ ፍለጋ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አስበኝ ፡ መድህኔ ጠግቤ ፡ እኖራለሁ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አስበኝ ፡ ሬድኤቴ ፍቅርህ ፡ መድሃኒት ፡ ነው ፡ ፈውስ ፡ ለሕይወቴ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ከአፌ ፡ አላወርድም ፡ ይህን ፡ ሥምክን አላርፍም ፡ አልረካም ፡ እስካገኝህ (፪x) የተመኘሁትን ፡ ያሰብኩትን ፡ ይዤ ግን ፡ አልረካሁኝም ፡ አለሁኝ ፡ ተክዤ ጐተራዬ ፡ አልሞላም ፡ ፍላጐቴ ፡ አልቆመ የውስጠቴን ፡ ርሃብ ፡ ይሄ ፡ አላተገበም ወደ ፡ አንተ ፡ እጠራለሁ ፡ ሙጥኝ ፡ እልሃለሁ ያገኘሁህ ፡ እለታ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ ሰው ፡ መልካም ፡ ምግብ ፡ በልቶ ፡ እንዲጠግብ ነፍሴ ፡ ትጠግባለኝ ፡ በክብርህ ፡ በግርማህ ሰው ፡ መልካም ፡ ምግብ ፡ በልቶ ፡ እንዲጠግብ ነፍሴ ፡ ትጠግባለኝ ፡ ጌታዋን ፡ ስታስብ ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ፍሰሃ ኢየሱስ ፡ ብኖር ፡ በበረሃ ኢየሱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ብርሃን ኢየሱስ ፡ ባልፍም ፡ በጨለማ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አስበኝ ፡ ሬድኤቴ ፍቅርህ ፡ መድሃኒት ፡ ነው ፡ ፈውስ ፡ ለሕይወቴ አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አስበኝ ፡ መድህኔ ጠግቤ ፡ እኖራለሁ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ በመጠበቂያዬ ፡ በማማዬ ፡ ሆኜ እጠብቅሃለሁ ፡ እንዳይህ ፡ አምኜ ዝለቴ ፡ ድካሜ ፡ ይወገድ ፡ አፍረቴ በሰፈሬ ፡ እንድታልፍ ፡ እንድትገባ ፡ ቤቴ ባላሰብኩት ፡ ሰዓት ፡ ባልጠበኩት ፡ ቦታ በጊዜ ፡ ሰሌዳ ፡ በአንተ ፡ አቆጣጠር የጠበኩህ ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ትመጣለህ ረሃቤን ፡ ጥማቴን ፡ ያኔ ፡ ታረካለህ የጠበኩህ ፡ ጌታ ፡ ድንገት ፡ ትመጣለህ ረሃቤን ፡ ጥማቴን ፡ አንተው ፡ ታረካለህ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ወዳጄ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ከአፌ ፡ አላወርድም ፡ ይህን ፡ ሥምክን አላርፍም ፡ አልረካም ፡ እስካገኝህ (፪x)