Loading
Singer
Updated 9/5/2026
እኔ ፡ ያወቅሁት ፡ ካወቅሁት ፡ ጀምሮ ታሪክ ፡ ሲለውጥ ፡ በአዲስ ፡ አሳምሮ ሰዎችም ፡ ሲሉ ፡ ሃዘኔን ፡ አስረሳኝ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳን አዝ፦ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ ጌታ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ አዳነኝ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ ልዩ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ አወጣኝ ፡ ከእሳት ፡ እያሉ ማን ፡ ያልወጣ ፡ አለ ፡ ከጭንቅ ፡ ከፍራቱ አንተን ፡ አስገብቶ ፡ ጌታ ፡ በሕይወቱ ተዐምረኛ ፡ ሃይለኛ ፡ ነህ ፡ የተጣለውን ፡ ታነሳለህ (፫x) ተአምረኛ ፡ ሃይለእኛ ፡ ነህ ፡ በፍቅር ፡ ልብን ፡ ትይዛለህ የታሰርኩበትም ፡ ሰንሰለት ፡ ረገፈ የእስር ፡ ቤቱ ፡ መዝጊያ ፡ ራሱ ፡ ተከፈተ አዳነኝጌታዬ ፡ መልአኩን ፡ ልኩ ነፍስም ፡ አልቀረኝ ፡ አይ ፡ አደራረጉ አዝ፦ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ ጌታ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ አዳነኝ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ ልዩ ፡ ነው ፡ ይክበር ፡ እያሉ እያሉ ፡ ሲመሰክሩ ፣ አወጣኝ ፡ ከእሳት ፡ እያሉ ማን ፡ ያልወጣ ፡ አለ ፡ ከጭንቅ ፡ ከፍራቱ አንተን ፡ አስገብቶ ፡ ጌታ ፡ በሕይወቱ ተዐምረኛ ፡ ሃይለኛ ፡ ነህ ፡ የተጣለውን ፡ ታነሳለህ (፫x) ተአምረኛ ፡ ሃይለእኛ ፡ ነህ ፡ በፍቅር ፡ ልብን ፡ ትይዛለህ እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለ ፡ እያሉ ወንድሞች ፡ በሆታ ፡ ስራህን ፡ ያወራሉ እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለ ፡ እያሉ እህቶች ፡ በዕልልታ ፡ አንተን ፡ ያደንቃሉ ፍቅርህን ፡ የቀመሱ ፡ በረከትህን ፡ ያዩ ከውስጥ ፡ ከልባቸው ፡ አንተን ፡ ያከብራሉ አንተን ፡ ያከብራሉ ፡ አንተን ፡ ያነግሳሉ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ እያሉ (፪x)