Loading
Singer
አዝ፦ ከአንተ ፡ የሚበልጥ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለም አንተ ፡ ብቻ ፡ አምላኬ/አንደኛ ፡ ዘለዓለም ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ (፪x) በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ አመሰግናለሁ በአንተ ፡ ሥም ፡ እጆቼን ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አነሳለሁ በቅበና ፡ በስብ ፡ እንደሚጠግቡት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ነፍሴ ፡ ትጠግባለች ፡ አምላኬ ፡ ያልኩትን አዝ፦ ከአንተ ፡ የሚበልጥ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለም አንተ ፡ ብቻ ፡ አንደኛ ፡ ዘለዓለም ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ ቅዱሳኑ ፡ ሁሉ ፡ እርሱን ፡ ወደዱት ፡ የእኔን ፡ ጌታ ፊተኛ ፡ ቀዳሚ ፡ ሆሆ ፡ አንደኛ ፡ አድርጉት ፡ ሆ አንተ ፡ ስትወደድ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ የእኔ ፡ ጌታ የወዳጄ ፡ ወዳጅ ፡ ልቤን ፡ ያረካኛል አዝ፦ ከአንተ ፡ የሚበልጥ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለም አንተ ፡ ብቻ ፡ አንደኛ ፡ ዘለዓለም ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ ዘለዓለም ፡ ተባረክልኝ ፡ ዘለዓለም ፡ ተወደስልኝ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ክብር ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና በጽድቅ ፡ የተሞላህ ፡ ሆሆ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና (፪x) ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ክብር ፡ ይሁን ፡ አምልኮ በጽድቅ ፡ የተሞላህ ፡ ሆሆ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነህኮ (፪x) ላመልክህ ፡ እወዳለሁ ላመልክህ ፡ እወዳለሁ ላመልክህ ፡ እወዳለሁ ፡ ላመልክህ (፪x) ላከብርህ ፡ እወዳለሁ ላከብርህ ፡ እወዳለሁ ላከብርህ ፡ እወዳለሁ ፡ ላከብርህ እስትንፋስ ፡ ያላቸው ፡ ፍጥረታት ፡ ሁሉ እንዴት ፡ አንተን ፡ አይተው ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ይላሉ በቋንቋቸው ፡ ሁሉም ፡ ያመሰግናሉ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ተመሥገን ፡ ይላሉ ክብር ፡ ይሁን ፡ ክብር ክብር ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና በጽድቅ ፡ የተሞላህ ፡ ሆሆ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና (፬x) ከክብርም ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ይሁንልህ ከምሥጋና ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ይሁንልህ ፡ ይሁንልህ ይሁንልህ ፡ ይሁንልህ (፬x)