Loading
Singer
ፍቅርን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ምህረትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ፡ ይቅርታን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ የማይለወጥ ፡ የአንተ ፡ ፍቅር የማትሰለች ፡ ሁልጊዜ ፡ ምትምር ይቅርታህ ፡ ብዙ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ጌታ ፡ እንተን ፡ አየሁ ፡ በምድር ፡ በሰማይ ትዕግሥትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ቸርነት ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ማስተዋል ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ አየሁኝ ፡ ጌታ ፡ ስትታገሰኝ በቸርነትህ ፡ ስትለግሰኝ ታስደንቃለህ ፡ ማስተዋል ፡ አለህ ሚመስልህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ እውነትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ዕውቀትን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ ጥበብን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ አንተ ፡ እውነት ፡ ነህ ፡ እውነተኛ ፡ ነህ ሁሉን ፡ ፈጥረሃል ፡ ሁሉን ፡ ታውቃለህ ጥበበኛ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ በምንም ፡ ነገር ፡ የማትረታ የዋህነት ፡ ከአንተ ፡ ለማር ፡ ኢየሱስ ትህትናን ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ መታዘዝ ፡ ከአንተ ፡ ልማር ፡ ኢየሱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ አትጨክንም ፡ አንተ ፡ የዋህ ፡ ነህ ዝቅ ፡ ማለትን ፡ ታውቅበታለህ እስከሞት ፡ ድረስ ፡ አንተ ፡ ታዘዝህ ኢየሱስ ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ ትማርካለህ