Loading
Singer
አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ኃያል ፡ ማንም ፡ የለም እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ ለዘለዓለም የሚቋቋምህ ፡ ኦሆ! ማንም ፡ የለም ስመ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም ይዘመርልህ ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ ነህ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ የተከበረ? በኃይሉ ፡ ሥልጣን ፡ ያልተደፈረ ከጥንት ፡ የነበረው ፡ ዛሬም ፡ ደግሞ ፡ ያለው እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ሥሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አልተለወጠም ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ብርቱ ፡ አምላክ ፡ ነው አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ኃያል ፡ ማንም ፡ የለም እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ ለዘለዓለም የሚቋቋምህ ፡ ኦሆ! ማንም ፡ የለም ስመ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም ምሕረት ፡ ዕውነቱ ፡ የተገለጠ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ያልተለወጠ ዕውነቱ ፡ ከምድር ፡ እስከ ፡ ሰማይ ፡ ያለው ሰላምን ፡ ለሕዝቡ ፡ ሁሌ ፡ የሚናገረው ያየነው ፡ ዕውነት ፡ እርሱ ፡ ታላቅ ፡ ነው ተወዳዳሪ ፡ ምን ፡ መሳይ ፡ አለው? አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ኃያል ፡ ማንም ፡ የለም እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ ለዘለዓለም የሚቋቋምህ ፡ ኦሆ! ማንም ፡ የለም ስመ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማን ፡ ብርቱ ፡ አለ? ሳይሰጋ ፡ ከቶ ፡ በክብር ፡ ያለ በተዘረጋ ፡ ክንዱ ፡ ሁሉን ፡ በሚችለው ተአምራት ፡ በመሥራት ፡ ስሙን ፡ ያስከበረው የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ሕያው ፡ ነው ኃያል ፡ ሥም ፡ ያለው ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፡ ነው አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ኃያል ፡ ማንም ፡ የለም እግዚአብሔር ፡ ብርቱ ፡ ለዘለዓለም የሚቋቋምህ ፡ ኦሆ! ማንም ፡ የለም ስመ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም