Loading
Singer
ለብቻዬ ፡ ልኖር ፡ ፈቃድህ ፡ ከሆነ ሌላው ፡ አይገደኝም ፡ ሕይወቴ ፡ ከዳኔ ሲሆን ፡ እስከንጋት ፡ ልታገልህና ስደደኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ ባርክና አዝ፦ ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x) ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x) ከመምበርከክ ፡ ብዛት ፡ በጸሎት ፡ ትግል ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ ጉልበቴ ፡ ይዛል እያነከስኩ ፡ ይሁን ፡ እከተልሃለሁ እጅህን ፡ ዘርጋብኝ ፡ በረከት ፡ እሻለሁ አዝ፦ ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x) ሊነጋ ፡ ሲጀምር ፡ ሰማዩም ፡ ሲቀላ ወደዚህ ፡ እሄዳለሁ ፡ ነፍሴ ፡ እንዲህ ፡ ዝላ ሕይወቴን ፡ ብቻ ፡ ባርክ ፡ ሌላ ፡ አልመኝም ሥም ፡ እንደው ፡ ቀሪ ፡ ነው ፡ ሥም ፡ አያድነኝም አዝ፦ ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x) ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x) እንደ ፡ ያዕቆብ ፡ ዛሬ ፡ ጩኸቴን ፡ ስማና ስደደኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ ባርክና ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ ስሜንም ፡ ለውጠው ሰው ፡ እንዳለው ፡ ሳይሆን ፡ አንተ ፡ እንደ ፡ ወደድከው አዝ፦ ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x) ካልባረከኝ ፡ አለቅህም (፪x)