Loading
Singer
በሞት ፡ ያልተሻረ ፡ በሞት ፡ ያልተገታ በሰማይም ፡ ቀጥሏል ፡ ክህነቱ ፡ የጌታ ሌሎቹ ፡ እንዳይኖሩ ፡ ሞት ፡ ከልክሏቸዋል ከነአሮን ፡ ክህነት ፡ የኢየሱስ ፡ ይበልጣል ካህኔ ፡ እንደመልከፄዴቅ : ካህኔ ፡ ለዘላለም ፡ ሹም ፡ ነህ ካህኔ ፡ ለእኔም ፡ ሕይወት ፡ መዳን : ካህኔ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ካህኔ ፡ በማይጠፋው ፡ ክህነት : ካህኔ ፡ በማይሽረው ፡ ሞት ካህኔ ፡ የምትማልድልኝ : ካህኔ ፡ ቆመህ ፡ በአብ ፡ ፊት ምን ፡ እላለሁ ፡ ከምስጋና ፡ ሌላ ምን ፡ እሰጣለሁ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በማታ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ ክበር (፪x) ካህኔ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ያለሀው : ካህኔ ፡ የነፍሴ ፡ ጠበቃ ካህኔ ፡ መከራዬ ፡ እንዲቆም : ካህኔ ፡ ሀዘኔ ፡ እንዲያበቃ ካህኔ ፡ የጥልን ፡ ግድግዳ : ካህኔ ፡ በሞት ፡ አፈረስህ ካህኔ ፡ ለበደሌ ፡ መስዋዕት : ካህኔ ፡ ደምህን ፡ አፈሰስህ በሞት ፡ ያልተሻረ ፡ በሞት ፡ ያልተገታ በሰማይም ፡ ቀጥሏል ፡ ክህነቱ ፡ የጌታ ሌሎቹ ፡ እንዳይኖሩ ፡ ሞት ፡ ከልክሏቸዋል ከነአሮን ፡ ክህነት ፡ የኢየሱስ ፡ ይበልጣል የካህናት ፡ አለቃ ፡ የበጎች ፡ እረኛ የእውነተኛዋ፡ ድንኳን : መካከለኛ በኔ ፡ ፈንታ ፡ የሞተ ፡ የሆነልኝ ፡ ቤዛ ነፍሴ ፡ በጣም ፡ ረክታለች ፡ ለእርሱ ፡ ስትገዛ መድህኔ ፡ የመቀበርያዬን : መድህኔ ፡ ጉድጓድ ፡ የደፈንከው መድህኔ ፡ የሕይወቴን ፡ ጨለማ : መድህኔ ፡ ገለል ፡ ያደረከው መድህኔ ፡ በሞትና ፡ በእኔ : መድህኔ ፡ መካከል ፡ ገብተህ መድህኔ ፡ ሕያው ፡ አደረከኝ : መድህኔ ፡ አንተ ፡ ተችሎህ ምን ፡ እላለሁ ፡ ከምስጋና ፡ ሌላ ምን ፡ እሰጣለሁ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በማታ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ ክበር (፪x) መድህኔ ፡ ዛሬስ ፡ ብርሃን ፡ ነው : መድህኔ ፡ ቀን ፡ ሆኖ ፡ ለነፍሴ መድህኔ ፡ ባንተ ፡ ተሰበረ : መድህኔ ፡ ለቅሶና ፡ ትካዜ መድህኔ ፡ ፍጻሜዬ ፡ እንዲያምር : መድህኔ ፡ የመጨረሻዬ መድህኔ ፡ አንተን ፡ መጠጋቴ : መድህኔ ፡ ልክ ፡ ነው ፡ ምርጫዬ ምን ፡ እላለሁ ፡ ከምስጋና ፡ ሌላ ምን ፡ እሰጣለሁ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር በማለዳ ፡ በቀትር ፡ በማታ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ ክበር (፪x)