Loading
Singer
የጽድቅ ፡ ሥራህን ፡ ጌታ ፡ ሰራህና በጨለማ ፡ ላሉ ፡ ፀሐይ ፡ ወጣችና ከዘለዓለም ፡ ጥፋት ፡ አንተ ፡ ያዳንካቸው በታዳጊነትህ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አላቸው (፪x) አዝ፦ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ያለህ ፡ የነበርህ ትልቁን ፡ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ የከበርህ ሥምህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ ይባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይንበርከክ የመስቀል ፡ ፍቅርህን ፡ ለሰው ፡ ይነግራሉ የቅድስናህን ፡ ክብር ፡ ያወራሉ በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ ታምነው ፡ ይኖራሉ የማዳን ፡ ክንድህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ያያሉ (፪x) አዝ፦ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ያለህ ፡ የነበርህ ትልቁን ፡ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ የከበርህ ሥምህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ ይባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይንበርከክ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥምህ ፡ የከበረ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ያማረ የሚመስልህ ፡ የለም ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ ከፍ ፡ ብለህ ፡ ንገሥ ፡ ግርማ ፡ ተሞልተህ (፪x) አዝ፦ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ያለህ ፡ የነበርህ ትልቁን ፡ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ የከበርህ ሥምህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ ይባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይንበርከክ ክብርህ ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ ይታይ ፡ አምላካችን ምላስም ፡ ይመስክር ፡ ታላቅነትህን በሰማይ ፡ በምድር ፡ ትሰለጥናለህ ሁሉም ፡ ከእግርህ ፡ በታች ፡ አንተ ፡ ትገዛለህ (፪x) አዝ፦ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ያለህ ፡ የነበርህ ትልቁን ፡ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ የከበርህ ሥምህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ ይባረክ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይንበርከክ (፫x)