Loading
Singer
የመከራ ፡ ናዳ ፡ ትከሻው ፡ የቻለው የድልን ፡ ጐዳና ፡ ሊያሳየኝ ፡ ብሎ ፡ ነው እስከመጨረሻው ፡ በአምላኬ ፡ ታምኜ ጌታን ፡ አየዋለሁ ፡ ምድር ፡ አፋፍ ፡ ላይ ፡ ሆኜ አዝ:- ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ የማታ ፡ የማታ ፡ ድሌን ፡ አገኛለሁ ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ የማታ ፡ የማታ ፡ ድል ፡ እቀዳጃለሁ ጊዜው ፡ ቢቆርቁር ፡ አንጀቴ ፡ ቢባባ ልቤ ፡ ቢርድብኝ ፡ ዓይኔ ፡ ቢያዝል ፡ እንኳ ሞትን ፡ ድል ፡ የነሳው ፡ ዛሬም ፡ ድል ፡ የእርሱ ፡ ነው ከእቅፉ ፡ ፈልቅቆ ፡ የሚጐዳኝ ፡ ማነው አዝ:- ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ የማታ ፡ የማታ ፡ ድሌን ፡ አገኛለሁ ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ የማታ ፡ የማታ ፡ ድል ፡ እቀዳጃለሁ ተስፋሽ ፡ አምላክሽ ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ አትፍሪ አምላክ ፡ ደጀኔ ፡ ነው ፡ ብለሽ ፡ ተናገሪ መከታሽ ፡ ከሆነ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ በዓለም ፡ አይገኝም ፡ አንቺን ፡ የሚረታ አዝ:- ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ የማታ ፡ የማታ ፡ ድሌን ፡ አገኛለሁ ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ የማታ ፡ የማታ ፡ ድል ፡ እቀዳጃለሁ በጐደለኝ ፡ ነገር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ሙላቴ በጥማቴ ፡ እርካታ ፡ በድካም ፡ ብርታቴ ከመጪው ፡ ፈተና ፡ እንዲያስጥለኝ ፡ አውቃለሁ ባያደርገው ፡ እንኳን ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እሞታለሁ አዝ:- ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ የማታ ፡ የማታ ፡ ድሌን ፡ አገኛለሁ ጌታ ፡ በሚያስችለኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ የማታ ፡ የማታ ፡ ድል ፡ እቀዳጃለሁ