Loading
ፊደል ፡ ተግጣጥሞ ፡ የቱ ፡ ቃል ፡ ገለጠህ ቃላት ፡ ተሰካክተው ፡ ምን ፡ ቢባል ፡ ተረከህ ያንተን ፡ ልክ ፡ አዋቂ ፡ አንተ ፡ እግዚዓብሔር ፡ ብቻ እራስህ ፡ ንገረኝ ፡ ምን ፡ እንድልህ ፡ ብቻ የተባልከው ፡ ሁሉ ፡ ካንተ ፡ በታች ፡ ሆኗል ለፍጥረት ፡ ሚበዛው ፡ ላንተ ፡ አቅም ፡ አንሶታል ያንተን ፡ ልክ ፡ አዋቂ ፡ አንተ ፡ እግዚዓብሔር ፡ ብቻ እራስህ ፡ ንገረኝ ፡ ምን ፡ እንድልህ ፡ ብቻ መጀመርያም ፡ መጨረሻም ፡ የሌለህ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛም ፡ ኋለኛም ፡ የሌለህ እግዚዓብሔር ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x) የእኔ ፡ ትልቅ ፡ አንተ ፡ ነህ የእኔ ፡ ጀግና ፡ አንተ ፡ ነህ ሁሉን ፡ በስርህ ፡ አስተዳዳሪ ፡ በላይ ፡ ለሁሉ ፡ ሁሉን ፡ ፈጣሪ የግዙፍ ፡ ግዙፍ ፡ የትልቅ ፡ ትልቅ ቃል ፡ በማይደፍረው ፡ የከፍታ ፡ ጥግ አንተ ፡ እግዚዓብሔር ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ትልቅ ፡ መሳዩን ፡ ትንሽ ፡ ያደረግህ ጀግና ፡ መሳዩን ፡ ያንበረከክህ ጠቢብ ፡ መሳዩን ፡ ሞኝ ፡ ያደረግህ ያለው ፡ መሳዩን ፡ ባዶ ፡ ያደረግህ የለም ፡ ያሉህ ፡ የሉም ዛሬም ፡ የሚሉህ ፡ ነገ ፡ አይኖሩም (፪x) ይገርመኛል ፡ ትጋታቸው ፡ የከንቱነት ፡ ጥበባቸው ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ሕይወት ፡ ማሰባቸው አንተው ፡ ባበጀኸው ፡ አእምሮ ባንተ ፡ ጥበብ ፡ ተቀምሮ እስትንፋስ ፡ ለግሰህ ፡ በእፍታህ ባምሳልህ ፡ ሰርተኸው ፡ ስታበቃ የለህም ፡ የሚልህ ፡ ማን ፡ ነው እኮ ፡ የለህም ፡ የሚልህ ፡ ማን ፡ ነው ለመኖርህ ፡ የእርሱም ፡ መኖር ፡ ምስክር ፡ ነው (፫x) ለመኖርህ ፡ የእኔም ፡ መኖር ፡ ምስክር ፡ ነው ሉዓላዊነት ፡ ከጥንት ፡ ከዓለማት ፡ በፊት ፡ የነበረ አለህ ፡ የለህም ፡ ቢባል ፡ ከመኖር ፡ ያልተገደበ እግዚዓብሔር ፡ አለህ ፡ በማደርያህ እግዚዓብሔር ፡ አለህ ፡ በዙፋንህ አለህ ፡ በማደርያህ አለህ ፡ በዙፋንህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.