Loading
Singer
ብላቴና ፡ ሳለሁ ፡ የመረጥከኝ ፡ አምላክ ለአንተ ፡ እንድዘምር ፡ ታማኝ ፡ አርገህ ፡ ቆጥረህ በሁለንተናዬ ፡ እንዳከብርህ ፡ አንተን ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ፈውሰው ፡ ሕይወቴን አዝ፦ እባክህ ፡ ኢየሱስ (፪x) ፡ ሕይወቴን ፡ ፈውስ/ቀይር ሰዎች ፡ እኔን ፡ ሲያዩ ፡ ስምህ ፡ እንዲቀደስ/እንዲከበር (፪x) እባክህ ፡ ባክህ ፡ እግዚአብሔር ሕይወቴን ፡ ቀይር ሕይወቴን ፡ ቀይር እባክህ ሕዝብህን ፡ ልትባርከው ፡ ስትሰጠኝ ፡ ፀጋ ከትላንቱ ፡ ይልቅ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ ለታይታ ፡ አይሁን ፡ መንፈሳዊነቴ አንተን ፡ እንዲገልጥህ ፡ መላው ፡ እኔነቴ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ አባቴ (፪x) ፡ ክበር ፡ በሕይወቴ በሁሉ ፡ ይገለጥ ፡ የሕይወት ፡ እድገቴ ስለእኔ ፡ ኃጢአት ፡ ደምህ ፡ ፈሶልኛል እራስህን ፡ ሰውተህ ፡ ሕያው ፡ አድርገኸኛል እኔ ፡ ግን ፡ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ተስኖኛል እጅህ ፡ ግን ፡ ከመጣ ፡ አድኖ ፡ ያስቀረኛል አዝ፦ እባክህ ፡ ኢየሱስ (፪x) ፡ ሕይወቴን ፡ ቀድስ አንተን ፡ ለተራቡ ፡ ቃልህን ፡ እንዳለ ሕያውና ፡ ቅዱስ ፡ መስዋዕት ፡ አድርጌ ለአንተ ፡ ሰውነቴን ፡ እንዳቀርብ ፡ አምላኬ በፍፁም ፡ መለወጥ ፡ ሕይወቴ ፡ ይገራ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ እንድፈራ አዝ፦ እባክህ ፡ እግዚአብሔር (፪x) ፡ ሕይወቴን ፡ ቀይር ደግሞም ፡ መጨረሻዬ ፡ በፊትህ ፡ እንዲያምር (፪x)