Loading
Singer
ወንድሞች ፡ በሕብረት ፡ ቢቀመጡ ፡ ቀርበው ለማነጽ ፡ የሚጠቅም ፡ የፀጋ ፡ ቃል ፡ ይዘው አፋቸውን ፡ ሲከፍቱ ፡ በክርስቲያን ፡ ቋንቋ ምንኛ ፡ ደስ ፡ ይላል ፡ ሲቀር ፡ አሉባልታ አዝ፦ ሕይወት ፡ ለተጠማ ፡ የምሥራች ፡ በሉ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ወደው ፡ ቢቀበሉ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ይሰበካል የሚያረካ ፡ ምንጭ ፡ ለሁሉም ፡ ተሰብኳል የመንፈስን ፡ ፍሬ ፡ አዝሎ ፡ በሕይወቱ የአምላክን ፡ ደራሲ ፡ አውቆ ፡ ማንነቱን ጌታን ፡ ሲያንፀባርቅ ፡ እስከ ፡ ዕለተ ፡ ሞቱ ከክበር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ ይለወጣል ፡ ቤቱ አዝ፦ ሕይወት ፡ ለተጠማ ፡ የምሥራች ፡ በሉ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ወደው ፡ ቢቀበሉ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ይሰበካል የሚያረካ ፡ ምንጭ ፡ ለሁሉም ፡ ተሰብኳል ሸክምን ፡ ለማራገፍ ፡ በመስቀሉ ፡ እግር ክርስቲያን ፡ ሲንበረከክ ፡ ልቡ ፡ ሲሰባበር ሚስጥሩን ፡ ለጌታ ፡ በእንባ ፡ አወያይቶ ተፅናንቶ ፡ ይነሳል ፡ በእምነት ፡ ተሞልቶ አዝ፦ ሕይወት ፡ ለተጠማ ፡ የምሥራች ፡ በሉ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ወደው ፡ ቢቀበሉ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ይሰበካል የሚያረካ ፡ ምንጭ ፡ ለሁሉም ፡ ተሰብኳል ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ሕብረቱ ፡ ጠንክሮ ሕይወት ፡ ሲስተካከል ፡ ግንኙነት ፡ ሰምሮ ኑሮ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ዓለምን ፡ ያስንቃል ለዛ ፡ አለው ፡ ይጥማል ፡ ቢመረጥ ፡ ይበጃል አዝ፦ ሕይወት ፡ ለተጠማ ፡ የምሥራች ፡ በሉ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ወደው ፡ ቢቀበሉ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ይሰበካል የሚያረካ ፡ ምንጭ ፡ ለሁሉም ፡ ተሰብኳል