Loading
Singer
ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ አንተ ፡ የልቤ ፡ ሆይ (፪x) አንዴ ፡ አስበኝና ፡ ማዳንህን ፡ ልይ (፪x) ክንዱ ፡ ወዴት ፡ አለ ፡ ብሎ ፡ ለሚለኝ (፪x) ለህዝብህ ፡ ጥያቄ ፡ ባክህ ፡ መልስ ፡ አርገኝ (፪x) አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ (፪x) አምላኬ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ እንጀራ ፡ እንደሆነ ፡ ጠግቤያለሁኝ የምድርን ፡ ቋጠሮ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ (፪x) ምነው ፡ ብትወርድ ፡ ምነው ፡ ብትፈርድ ፡ ለሃገሬ ፡ ለምድሬ የፈሰሰው ፡ እንባ ፡ ቢታበስ ፡ የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ቢታደስ ምነው ፡ ብትወርድ ፡ ምነው ፡ ብትፈርድ ፡ ለሃገሬ ፡ ለምድሬ ተራራው ፡ በፊትህ ፡ ቢናወጥ ፡ ስምህ ፡ ለጠላቶች ፡ ቢገለጥ መልሰኛ ፡ ፈውስ ፡ አድርገህ ፡ ለሃገሬ ፡ ህመምተኛ ቀድሰኛ ፡ እንድሆን ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ ተቆጥተህ ፡ ፊትህን ፡ አትደብቅብኝ ደክሞኝ ፡ ሳለ ፡ ጠላቴ ፡ እንዳይወድቅብኝ በፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ የቆመ ፡ ለእንጀራ ፡ ያልኖረ (፪x) የቤትህ ፡ ቅናት ፡ የሚበላው ፡ ስሙን ፡ የቀበረ (፪x) የልብህን ፡ ቁጣ ፡ ትኩሳት ፡ የሚያበርድልህ (፪x) እንዲህ ፡ ዐይነት ፡ ጨካኝ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ኃይልህን ፡ ሞልተህ (፪x) ከዚያ ፡ በኋላማ ፡ ስምህን ፡ አክብረህ ፡ ትመላለሳለህ ፡ መስርአት ፡ ሳይከብድህ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ (፪x) አምላኬ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ እንጀራ ፡ እንደሆነ ፡ ጠግቤያለሁኝ የህዝቤን/የምድሬን ፡ ቋጠሮ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ (፪x) ምነው ፡ ብትወርድ ፡ ምነው ፡ ብትፈርድ ፡ ለሃገሬ ፡ ለምድሬ የፈሰሰው ፡ እንባ ፡ ቢታበስ ፡ የፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ቢታደስ ምነው ፡ ብትወርድ ፡ ምነው ፡ ብትፈርድ ፡ ለሃገሬ ፡ ለምድሬ ተራራው ፡ በፊትህ ፡ ቢናወጥ ፡ ስምህ ፡ ለጠላቶች ፡ ቢገለጥ መልሰኛ ፡ ፈውስ ፡ አድርገህ ፡ ለሃገሬ ፡ ህመምተኛ ቀድሰኛ ፡ እንድሆን ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ ተቆጥተህ ፡ ፊትህን ፡ አትደብቅብኝ ደክሞኝ ፡ ሳለ ፡ ጠላቴ ፡ እንዳይወድቅብኝ በምድሬ ፡ እንዳትሰራ ፡ እንዳትከብር ፡ የከለከልኩኝ (፪x) አንካሳ ፡ የሕይወት ፡ ማንነት ፡ ያለኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ (፪x) አሁን ፡ ግን ፡ በምህረት ፡ ዐይንህ ፡ አይተኸኝ (፪x) የተጨነቀውን ፡ ህዝብህን ፡ ስጠኝ (፪x) ኢየሱስ ፡ እባክህ ፡ ነክቼህ ፡ ንካኝ ኃይልህ ፡ እስኪወጣ ፡ ልበልህ ፡ ሙጥኝ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ (፪x) አምላኬ ፡ ክብርህ ፡ ራበኝ እንጀራ ፡ እንደሆነ ፡ ጠግቤያለሁኝ የህዝቤን/የምድሬን ፡ ቋጠሮ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ (፪x) ህዝቤን ፡ ስጠኝ ፡ እንደፈቃድህ ፡ አውለኸኝ ፡ ህዝቤን ፡ ስጠኝ ህዝቤን ፡ ስጠኝ ፡ በቅድስናህ ፡ አውለከኝ ፡ ህዝቤን ፡ ስጠኝ ህዝቤን ፡ ስጠኝ (፬x)