Loading
Singer
አዝ፦ ህልሜ ፡ ሰምሯል ፡ በልጅነት ፡ ያየሁት በውሃ ፡ ውስጥ ፡ ያለፍኩለት ፡ በእሳት አልቀረሁም ፡ እንዳሰበው ፡ ያ ፡ ጠላቴ ሁሉን ፡ አለፍኩ ፡ አቅም ፡ ሆኖኝ ፡ ቸር ፡ አባቴ (፪x) ሰምቼ ፡ ድላድ ፡ የነፃነት ፡ ፋና ከሞት ፡ አምልጫለሁ ፡ ከድቅድቅ ፡ ጨለማ የአዲስ ፡ ነገር ፡ ጅምር ፡ የታሪክ ፡ ምዕራፍ ጌታ ፡ ከፍቶልኛል ፡ የበረከት ፡ ደጃፍ አዝ፦ ህልሜ ፡ ሰምሯል ፡ በልጅነት ፡ ያየሁት በውሃ ፡ ውስጥ ፡ ያለፍኩለት ፡ በእሳት አልቀረሁም ፡ እንዳሰበው ፡ ያ ፡ ጠላቴ ሁሉን ፡ አለፍኩ ፡ አቅም ፡ ሆኖኝ ፡ ቸር ፡ አባቴ (፪x) በእውነት ፡ የታመንክ ፡ ነህ ፡ ከቃልህ ፡ አንድ ፡ አይወድቅም ልትሰራ ፡ ተነስተህ ፡ አቅም ፡ አጥተህ ፡ አታውቅም የተረሳሁ ፡ ሲመስለኝ ፡ ስባል ፡ አስታዋሽ ፡ የለው አንተ ፡ ስትራራልኝ ፡ አዲስ ፡ ነገርን ፡ አየሁ ወደኋላ ፡ አልልም ፡ ያየልኝ ፡ አለና አምላኬ ፡ ከፊቴ ፡ ቀድሞኝ ፡ ወጥቷልና ልሂድ ፡ ልዘርጋ ፡ እንጂ ፡ ዱሩንም ፡ ልመንጥር አለ ፡ ካለሁበት ፡ የሚበልጥ ፡ ክብር (፪x) አዝ፦ ህልሜ ፡ ሰምሯል ፡ በልጅነት ፡ ያየሁት በውሃ ፡ ውስጥ ፡ ያለፍኩለት ፡ በእሳት አልቀረሁም ፡ እንዳሰበው ፡ ያ ፡ ጠላቴ ሁሉን ፡ አለፍኩ ፡ አቅም ፡ ሆኖኝ ፡ ቸር ፡ አባቴ (፪x)