Loading
Singer
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ሃሳቤን ፡ ጥላለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ጭንቀቴን ፡ ረሳለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ሰላሜ ፡ ሙሉ ፡ ነው ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ደስታዬ ፡ ፍፁም ፡ ነው ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ሃዘኔን ፡ ተዋለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ጉድለቴን ፡ ረሳለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ለሊቱም ፡ ይነጋል ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ባዶዬ ፡ ይሞላል አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ ህልሜ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ኦሆሆ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ውዴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ኦሆሆ ውዴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሳየው ፡ ተራራው ፡ ይናዳል ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሳየው ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ እኔ ፡ አይላለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ጠላቴን ፡ ጥላለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ድካሜን ፡ ረሳለሁ ክንድህን ፡ ተደግፌ ፡ በአንተ ፡ እመካለሁ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ከቶ ፡ የለኝ ፡ ከልካይ የአባትነት ፡ ፍቅርህ ፡ ልጅነቴ ፡ ገብቶኝ አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ ህልሜ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ኦሆሆ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ውዴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ኦሆሆ ውዴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ ጩኸቷ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መሆን ፡ ሁልጊዜ ፡ ናፍቆቷ ፊትህን ፡ እያየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ላመልክህ ክብርህን ፡ እያየሁ ፡ ወድቄ ፡ ላደንቅህ አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ ህልሜ ፡ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ፡ አሃሃ ዙፋንህን ፡ ማየቴ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ፡ ኦሆሆ ክብርህን ፡ ማየቴ ዙፋንህ ፡ ሥር ፡ ሆኜ ፡ እኔም ፡ አሰግዳለሁ ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ እላለሁ ባልተሰማ ፡ ቅኔ ፡ ያኔ ፡ አቀኛለሁ ከመላዕቶችህ ፡ ጋር ፡ አብሬ ፡ አሰግዳለሁ አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ ህልሜ ፡ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ክብርህን ፡ ማየቴ ፡ ኦሆሆ ክብርህን ፡ ማየቴ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ፡ አሃሃ ዙፋንህን ፡ ማየቴ የሚጠፋው ፡ አልፎ ፡ የሚጠፋውን ፡ ስለብስ እሩጫዬ ፡ አልቆ ፡ ዘለዓለሜ ፡ ስደርስ ያኔ ፡ የፍቅር ፡ ፊትህን ፡ ፊት ፡ ለፊቴ ፡ ሳየው በምን ፡ ቋንቋ ፡ ይሆን ፡ መውደዴን ፡ ምገልጸው አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ ህልሜ ፡ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ክብርህን ፡ ማየቴ ፡ ኦሆሆ ክብርህን ፡ ማየቴ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ፡ ኦሆሆ ክብርህን ፡ ማየቴ