Loading
Singer
በምንም ፡ አልሰጋም ፡ ልቤም ፡ አይደነግጥ በሆነው ፡ ባልሆነው ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ መናወጥ ስለ ፡ ነገ ፡ እያሰብኩ ፡ እኔ ፡ አልጨነቅም እግዚአብሔር ፡ ሳያውቀው ፡ በእኔ ፡ የሚሆን ፡ የለም አዝ፦ እኔማ ሀሳቤን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ ሀዘኔን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ ሸክሜም ፡ ይኸው ፡ በፊትህ ናፍቆቴ ፡ መኖር ፡ በእረፍትህ (፪x) ለማይሞልውና ፡ ለዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ታዲያ ፡ ለምንድን ፡ ነው ፡ መጨነቅ ፡ መሸበር ትላንት ፡ ዛሬ ፡ አይደል ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ ጠላት ፡ ይስማው ፡ እንጂ ፡ ድሌን ፡ ዘምራለሁ አዝ፦ እኔማ ሀሳቤን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ ሀዘኔን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ ሸክሜም ፡ ይኸው ፡ በፊትህ ናፍቆቴ ፡ መኖር ፡ በእረፍትህ ምክኒያቱ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ዛሬን ፡ ለመኖሬ ስንቱን ፡ በእርሱ ፡ አልፌ ፡ ስንቱን ፡ ተሻግሬ እግዚአብሔር ፡ ስላለኝ ፡ ነገንም ፡ ደፍራለሁ ዘመኑን ፡ ዋጅቼ ፡ በቀኑ ፡ ኖራለሁ አዝ፦ እኔማ ሀሳቤን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ ሀዘኔን ፡ በአንተ ፡ ጥያለሁ ሸክሜም ፡ ይኸው ፡ በፊትህ ናፍቆቴ ፡ መኖር ፡ በእረፍትህ ነፍሴ ፡ አትማረሪ ፡ አታስጨንቂኝ እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ነው ፡ የሚሆንልኝ በሰው ፡ አልታመን ፡ እኮ ፡ ሥጋ ፡ ለባሹን ጌታ ፡ ይሰጠኛል ፡ መከናወኔን እ ፡ ነፍሴ ፡ አትማረሪ እ ፡ አታስጨንቂኝ እ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ነው ተዪኝ ፡ የሚሆንልኝ እ ፡ በሰው ፡ አልታመንኩ እ ፡ ሥጋ ፡ ለባሹን እ ፡ ጌታ ፡ ይሰጠኛል ተዪኝ ፡ መከናወኔን