Loading
Singer
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ ያ ፡ አስፈሪው ፡ ግርማህ ፡ ለአንዳፍታ ፡ ተቀይሮ ጌታነትህ ፡ ክብር ፡ በባርነት ፡ ተመንዝሮ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ከሆንክ ፡ አራስህን ፡ አድን ፡ ሲሉህ የእኔን ፡ ቂም ፡ በእንተ ፡ በመስቀል ፡ ሲወጡ ነፍሴ ፡ ወጣች ፡ ከእስራቱ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ የሰው ፡ አንቆቅልሽ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ምላሽ ፡ ሲያገኝ ለተገፊዎቹም ፡ ችሎት ፡ ቀርበህ ፡ ስትል ፡ ይግባኝ በአንተ ፡ መገፋት ፡ ግን ፡ ሰማይ ፡ ምድር ፡ ዝም ፡ ሲሉ ሃይልህ ፡ አስኪገለጥ ፡ አጅግ ፡ ቢያቃልሉህ በክንድህ ፡ ሲዖል ፡ ተጣሉ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ የክፋቴ ፡ ብዛት ፡ በሰው ፡ አፍ ፡ መርገም ፡ ሆኖ ወሬ ፡ ለሚሰማ ፡ ለሚያይም ፡ አይን ፡ አስጨፍኖ በሰፈሬ ፡ ስታልፍ ፡ ያንን ፡ ስድቤን ፡ ስትሸከም በቁጣው ፡ ስትደርቅ ፡ ነፍሴን ፡ ለማለምለም ከፍ ፡ በል ፡ ለዘለዓለም አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ ቆሞ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ከህያዋን ፡ መቀላቀል በሚመጣውም ፡ አለም ፡ ብቤትህ ፡ አኔን ፡ ስትቀበል ከዚያም ፡ አልፎ ፡ የጓዳዬ ፡ መከራ ፡ ሲረሳ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ቀረ ፡ ያ ፡ አበሳ ክበር ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሲሆን ፡ ጠላቶች ፡ ዋሹብህ የቁጣቸው ፡ ግለት ፡ በላይህ ፡ በረደብህ ምን ፡ ልበል ፡ ታዲያ ፡ ውዴ ፡ ምንስ ፡ ልክፈልህ በአንተ ፡ አረፈች ፡ ነፍሴ ፡ ለዘላለም ፡ ታመስግንህ