Loading
ጌታ ፡ ለስሜቴ ፡ ለሥጋዬ ለራሴ ፡ ለፍላጐቴ አትስጠኝ(፫) ፡ ቸሩ ፡ አባቴ ሃሳቤን ፡ ፈውሰው(፪) ክፋትን ፡ ለማድረግ ፡ ቁጭ ፡ ብዬ ፡ ባስበው በመኝታዬ ፡ ሆኜ ፡ ባሰላስለው ነግቶ ፡ ላላደርገው ፡ ዋስትና ፡ የለኝም ኃይልም ፡ በእጄ ፡ ነው ፡ ከቶ ፡ አያቅተኝም ሃሳቤን ፡ ፈውሰው (፪) ክፉ ፡ አድራጊዎችን ፡ አንተ ፡ ትጠላለህ የጠማማውን ፡ መንገድ ፡ ትቃወመዋለህ አልሁንብህ ፡ ጌታ ፡ እንደምትጠላቸው የድርጊቴ ፡ ምንጩን ፡ ሃሳቤን ፡ ፈውሰው ሃሳቤን ፡ ፈውሰው (፪)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.