Loading
Singer
ሃሩሩ ፡ በረደ ፡ ጥላ ፡ በዝቶ ከጥሜም ፡ እረካሁ ፡ ውኃ ፡ ፈልቆ በቃ ፡ ሲል ፡ አበቃ ፡ መጨነቄ አሻገርከኝ ፡ ያንን ፡ ዘመን ፡ ጌታዬ አዝ፦ ያላለፍኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ ያልወጣሁት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ ያልወረድኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ ያልተሻገርኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ ተመሥገን ፡ በአንተ ፡ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ አለፍኩት (፬x) ሁልጊዜ ፡ ይነገር ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ነገር ስለ ፡ አንተ ፡ ዝና ፡ እስቲ ፡ ይወራ ያለፈ ፡ ይናገር ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ነገር ስለ ፡ አንተ ፡ ዝና ፡ እስቲ ፡ ይወራ አልተለየኸኝም ፡ በጭንቀቴ ደግፈህ ፡ አቆምከኝ ፡ መድኃኒቴ አጸናኸው ፡ እግሬን ፡ እንደ ፡ ዋላ ፡ እግር ከልቤ ፡ ልበልህ ፡ ተመሥገን አዝ፦ ያላለፍኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ ያልወጣሁት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ ያልወረድኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ ያልተሻገርኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ ተመሥገን ፡ በአንተ ፡ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ አለፍኩት (፬x) ሳስበው ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ዞር ፡ ብዬ ከችግር ፡ የተነሳ ፡ ተጨንቄ ማን ፡ ያሳልፈኛል ፡ ያልኩትን አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ያሳለፍከኝ ፡ ጌታዬ አዝ፦ ያላለፍኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ ያልወጣሁት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ ያልወረድኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ጌታ ያልተሻገርኩት ፡ ምን ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ኢየሱስ ተመሥገን ፡ በአንተ ፡ ሁሉን ፡ ችዬ ፡ አለፍኩት (፬x) ሁልጊዜ ፡ ይነገር ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ነገር ስለ ፡ አንተ ፡ ዝና ፡ እስቲ ፡ ይወራ ያለፈ ፡ ይናገር ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ነገር ስለ ፡ አንተ ፡ ዝና ፡ እስቲ ፡ ይወራ (፪x)