Loading
Singer
አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሁ ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ (፪x) እያሉ ፡ ቅዱሳን ፡ ሲያዜሙ ፡ ሰምቼ አብሪያቸው ፡ ዘመርኩ ፡ በግናን ፡ ቃኝቼ አዎ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ (፪x) ኢየሱስ ፡ የለም ፡ የሚመስልህ ባለ ፡ ጠጋ ፡ በገንዘቡ ፡ ይመካል ሰዎችንም ፡ በዚሁ ፡ ይለካል በቁጥር ፡ አያለሁ ፡ ብርቱ ፡ ሳይበላ ከሞት ፡ ይጠራል ፡ ትቶለት ፡ ለሌላ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታዬ ፡ የዘለዓለም ፡ ነህ እናምልክህ ፡ ታዋጣናለህ (፪x) አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ ፡ አሜን ፡ አሜን ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሁ ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ እያሉ ፡ ቅዱሳን ፡ ሲያዜሙ ፡ ሰምቼ አብሪያቸው ፡ ዘመርኩ ፡ በግናን ፡ ቃኝቼ አዎ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ከማንም ፡ በላይ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ የለም ፡ የሚመስልህ ሥልጣን ፡ ዕውቀት ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ይሻራል የእኔ ፡ ጌታ ፡ ግን ፡ እንደገዛ ፡ ይኖራል የዚህ ፡ ዓለም ፡ ክብር ፡ እኔን ፡ አያጓጓኝ ዘለዓለማዊ ፡ ቆይቷል ፡ ከገባኝ ኃያላን ፡ ነን ፡ ያሉ ፡ እንደምን ፡ ተሞኙ የሕይወትን ፡ ጌታ ፡ ሳያገኙ (፪x) አዝ፦ ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሁ ሃሌሉያ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ (፪x) እያሉ ፡ ቅዱሳን ፡ ሲያዜሙ ፡ ሰምቼ አብሪያቸው ፡ ዘመርኩ ፡ በግናን ፡ ቃኝቼ አዎ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ (፪x) ኢየሱስ ፡ የለም ፡ የሚመስልህ የትም ፡ አልሄድ ፡ እርዳታን ፡ ፍለጋ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ሁሌ ፡ ባለጠጋ ደስ ፡ እያለኝ ፡ በቤቱ ፡ እኖራለሁ ምን ፡ ጐድሎብኝ ፡ እርሱን ፡ አግኝቻለሁ እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ ስላላገኘን ቀንም ፡ ሌትም ፡ እናከብርሃለን (፪x) እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ ስላላገኘን ዛሬም ፡ ነገም ፡ እናከብርሃለን ለዘለዓለም ፡ እናከብርሃለን (፫x)